የደቡብ ክልል ባህልና ቱሪዝም ቢሮ ኃላፊ አቶ ኃይለማሪያም ተስፋዬ "ያሆዴ" በዓል ላይ እንዲታደሙ የቀረበላቸውን ጥሪ ተቀበሉ

የደቡብ ክልል ባህልና ቱሪዝም ቢሮ ኃላፊ አቶ ኃይለማሪያም ተስፋዬ የሀዲያ የዘመን መለወጫ የሆነው "ያሆዴ" በዓል ላይ እንዲታደሙ የቀረበላቸውን ጥሪ ተቀብለዋል።

የያሆዴ በዓል ጥሪ አስተላላፊ ኮሚቴ አባላት የደቡብ ክልል ባህልና ቱሪዝም ቢሮ ተገኝተው መስከረም 14 2015 ዓ.ም በልዩ ድምቀት በሚከበረው የሀዲያ ዘመን መለወጫ ያሆዴ በዓል ላይ የደቡብ ክልል ባህልና ቱሪዝም ቢሮ ኃላፊ አቶ ኃይለማሪያም ተስፋዬ እንዲታደሙ ጥሪ አድርሰዋል።

Share this Post