በሆሳዕና ከተማ የጃሎ ናራሞ ቀበሌ ከባለድርሻ አካላት ጋራ በመሆን በየመንገድ ዳር የሚቸረቸረዉን ህገ-ወጥ ቤንዚንና ጊዜ ያለፈበትን የመጠጥ ምርቶችን በቁጥጥር ሥር አዋሉ ።

በሆሳዕና ከተማ የጃሎ ናራሞ ቀበሌ ከባለድርሻ አካላት ጋራ በመሆን በየመንገድ ዳር የሚቸረቸረዉን ህገ-ወጥ ቤንዚንና ጊዜ ያለፈበትን የመጠጥ ምርቶችን በቁጥጥር ሥር አዋሉ ።

የሆሳዕና ከተማ አስተዳደር መንግስት ኮሙኒኬሽን ጉዳዮች ጽ/ቤት ነሐሴ 23/2014ዓ.ም

በሆሳዕና ከተማ ጃሎ-ናራሞ ቀበሌ ንግድና ገቢያ ልማት ጽ/ቤት ኃላፊ አቶ መኩሪያ ባቾሮ እንደገለፁት ህገ-ወጥ ንግድን ለመቆጣጠር ከባለድርሻ አካላት ጋር በመሆን ባደረጉት ዘመቻ ከ13 ሺ ብር በላይ የሚገመት የቤንዚን ክምችትንና ጊዜ ያለፈበትን የህፃናት ዮዮ እና የተለያዩ የለስላሳ መጠጦችን በየሱቁ በመዘዋወር ባደረጉት ክትትልና ፊተሻ ቁጥጥር ሥር መዋሉን ጠቅሰው ህብረተሰቡም እንዲህ ዓይነቱን ህገ-ወጥ ድርጊት በመጠቆምና በማጋለጥ የበኩላቸውን አስተዋጽኦ እንዲያደርጉ አሳስበዋል ።

በሆሳዕና ከተማ የጀሎናራሞ ቀበሌ ዋና አስተዳዳሪ አቶ አለሙ ባሻና የቀበሌው ፖሊሲ ጽ/ቤት አዛዥ/ዋና ኢንስፔክተር ከሣውን ታኪሶ በየበኩላቸው መንግስት የዋጋ ንረትን ለመቆጣጠር እየሠራ ባለበት ወቅት ላይ ህገ-ወጥ ንግድን ለመቆጣጠር ድንገተኛ ፍተሻ ባደረጉበት የተለያዩ ህገ-ወጥ የንግድ ዕቃዎችን መያዛቸውን ጠቁመው በርካታ ጎዳናዎች ላይ ቤንዚን መያዛቸውን ገልፀው ይህ ዓይነቱ የክትትል ሥራ በቀጣይ ተጠናክሮ ሊቀጥል እንደሚገባና ህብረተሰቡም ከመንግሥት ጎን በመቆም የዋጋ ንረትን ለመቆጣጠር ከሚመለከታቸው አካላት ጎን በመሆን የበኩላቸውን እንዲወጡ ጥሪ አቅርበዋል ።

አክለውም ኃላፊዎቹ ጊዜ ያላፈባቻውን የመጣጥ ምርቶችን ህብረተሰቡ መግዛትም ሆነ መሸጥ በህግ የሚያስቀጣ ወንጀል መሆኑን አውቀው መገበያየት እንደሚገባ አሳስበዋል ።

 

 

+12

93Mulatu Sule Ertiro, Wondimu Defar and 91 others

11 Comments

8 Shares

Like

Comment

Share

Share this Post