በበዓሉ አከባበር ላይ የመንግስት የስራ ኃላፊዎችና ሰራተኞች፣ በተገኙበት በደማቅ ሁኔታ ተከብሯል።
በፕሮግራሙ መክፈቻ የወረዳው ዋና አስተዳደር አቶ ደመቀ በዶሬ የእንኳን አደረሳችሁ መልዕክት በማስተላለፍ ፕሮግራሙን ከፍቷዋሉ፥
ያሆዴ በዓልን ምክንያት በማድረግ የወረዳ በ/ቱ ጽ/ቤት ኃላፊ ወ/ሮ ሙሉነሽ ዱናጎ ባስተላለፉት መልዕክት እንኳን ለሀዲያ ብሔር ዘመን መለወጫ ያሆዴ በዓል በሰላም አደረሳችሁ በማለት በዓሉ ለሁሉም የህብረተሰብ ክፍል ለልጆች ለአባቶች ለእናቶች የራሳቸው ድርሻ ያለ መሆኑን በማስገንዘብ ከቅድማ ዝግጅት ጀምሮ እስከ መባቻ ድረስ ያለውን ይህንን በዓል ለአለም ህዝብ ለማስተዋወቅና በዓለም በማይዳሰሱ ቅርሶች ለማስመዝገብ ጥረት በመደረግ ላይ የለ ስለሆነ ሁለችንም በዓሉን በአዲስ መንፈስና በመልካም ምኞት ልናከብረዉ ይገባል ብለዋል።
የሌሞ ወረዳ ወረዳ የመንግስት ዋና ተጠሪ አቶ ኑራዲን አቡሻ እንኳን ለሀዲያ ብሔር ዘመን መለወጫ ያሆዴ በዓል በሰላም አደረሳችሁ በማለት የያሆዴ በዓል የተለያ ትርጉምና መገለጫ ለሀዲያ ያለ እንደሆነ ገልጸው በሀዲያ ዞን ሆሳዕና ሀዲይ ነፈራ ዕለተ ቅዳሜ 14/01/2015 ዓ.ም የበዓሉ ማጠቃለያ በድምቀት ስለሚከበር ሁሉም የህብረተሰብ ክፍል በፕሮግራሙ እንድተዳም መልዕክታቸውን አስቀምጠዋሉ።
ዘገባው፦ የወረዳው ብልጽግና ፓርቲ ቅ/ጽ/ቤት ሚዲያና ኮሚዩኒኬሽን ነው።