የሆሳዕና ከተማ አስተዳደር የሥራ አስፈፃሚ አመራር አካላት የዉሃና አስፋልት መንገድ መሰረተ-ልማቶች ጉብኝት አድርገዋል ።

የሆሳዕና ከተማ መንግስት ኮሙኒኬሽን ጉዳዮች ጽ/ቤት ህዳር 02/2015 ዓ.ም

የሆሳዕና ከተማ አስተዳደር ከንቲባ አቶ ሊሬ ጀማልና የሆሳዕና ከተማ ዉሃ አገልግሎት ድርጅት ሥራ-አስኪያጅ አቶ ሙልጌታ ዓለሙ በየበኩላቸው እንደገለፁት በሀይሴ ለሜጃ እየተገነባ ያለው የንፁህ የመጠጥ ዉሃ አቅርቦት ፕሮጀክት የሥራ ዉል በተገባ በጊዜ ሠሌዳ የቁፋሮና የዝርገታ ሥራ በፍጥነት እየተሠራ ቢሆንም በስምንቶ የአቅርቦት ችግር ምክንያት የግንባታ ሥራ ኢንደይዘገይ ከወዲሁ ባለድርሻ አካላት በመደጋገፍ መሥራት እንደሚገባ አሳስበዋል ።

አክለውም ከንቲባ በከተማው የ14.134 ኪ.ሜ የዉስጥ ለዉስጥ ከኮንክሪት አስፋልት ኃላፊነቱ የተወሰነ ተቆራጭ ፕሮጀክት የመንገድ መሠረተ የልማትም ውል በተገባ የጊዜ ሠሌዳ መሠረት የግንባታ ሥራ አልቆ የመንገድ ችግሮች ተፈተው ለማህበረሰብ አገልግሎት መስጠት እንዲችል በበቅ ሰው ኃይል፣ ተሽከርካሪዎችና ማቴሪያል ተደግፎ ግንባታ እንዲያፋጥኑ አሳስበዋል ።

Share this Post