የሆሳዕና ከተማ አስተዳደር ከንቲባ አቶ ዳዊት ጡምደዶ ባስተላለፉት መልዕክት በሀገራችን በጠቅላይ ሚንስትር ዶ/ር አብይ አህመድ ኢንሼቲቭ <በጎነት ለኢትዮጵያ ከፍታ > በሚል መሪቃል ለተቸገሩ ወገኖች የሚደረገው ድጋፍ ተጠናክሮ መቀጠሉን ገልፀው ኢትዮ -ቴሌኮም ለአረጋውያን ማዕከል ግንባታ ለሠጠው ድጋፍ ምስጋና በማቅረብ ግንባታው ለማጠናቀቅ በጎ አድራጊ ግለሰቦችና ድርጅቶች ድጋፋቸውን እንዲቀጥሉ አሳስበዋል ።
አክለውም የከተማው አስተዳደር ለአረጋውያንና ለአቅመ ደካሞች የሚያደርገው ድጋፍ አጠናክሮ እንዲቀጥልም አቶ ዳዊት ጠቁመዋል ።
በኢትዮ-ቴሌኮም የሆሳዕና ዲስትሪክት ሥራአስኪያጅ ዶ/ር ዓለማየሁ አሰፋ በበኩላቸው ኢትዮ -ቴሌኮም "በጎነት"የሚል መርሃ ግብር በየዓመቱ ተግባራዊ በማድረግ ተቋማዊ ማህበራዊ ከኃላፊነቱን በዘላቂነት እየተወጣ እንደሚገኝ በመግለፅ በተጠናቀቀው የበጀት
ዓመት በሀገር ደረጃ በ39 የበጎ አድራጎት ተቋማት ለሚገኙ 13ሺ 674 ድጋፍ ለሚሹ ወገኖች ከ47.8ሚሊየን ብር በላይ የገንዘብ ድጋፍ ማድረጉን ተናግረዋል ።
በሜሪጆይ ኢትዩጵያ የሆሳዕና አስተባባሪ ወ/ሮ አሰለፈች አሰፋ በሰጡት አስተያየት በከተማው ሆቴሎችና ምግብ ቤቶች በማስተባበር ለ40አረጋውያን የቤት ለቤት የምገባ ፕሮግራም እየተካሄደ መሆኑን ገልፀው ኢትዮ -ቴሌኮም ላደረገው ድጋፍ ምስጋና አቅርበዋል ።
የሆሳዕና ከተማ መንግስት ኮሙኒኬሽን ጉዳዮች ጽ/ቤት ነሐሴ 30/2017ዓ.ም
በነስሩ ባደዢ