የሆሳዕና እናት ቃለ-ህይወት ቤተክርስቲያን የ2018 አዲሱን የዘመን መለወጫ በዓል ምክንያት በማድረግ ከ110 በላይ የድሃ ድሃ የህብረተሰብ ክፍሎች የምግብ ዱቄትና የተለያዩ ድጋፎች ማድረጓ ተገለፀ ።

አክለውም ከድጋፎቹ መካከል ለእያንዳንዱ ቤተሰብ የ30 ኪሎ ግራም የምግብ ዱቄትና አንድ ሊትር ዘይት፣ አልባሳት እንደሚገኙበት ገልፀው ሙሉ ወጪ በመሸፈን ለ75 ህጻናት የትምህርት ቁሳቁስ ድጋፍ እንደሚደረግላቸውም ጠቁመዋል ።

በቤተክርስቲያኗ የፍቅርና ርህራሄ ዘርፍ አስተባባሪ አቶ ሙሉፀጋ ተስፋዬ በበኩላቸው ቤተክርስቲያኗ የድሃ ድሃ የህብረተሰብ ክፍሎች ለማገዝ ልጆችን ማስተማር ፣አረጋዊያን መጦር፣ራስ ማስቻል ማቋቋም ፣አካል ጉዳተኞችን መንከባከብና ልዩ ልዩ ድጋፎች ላይ ትኩረት በማድረግ እንደምትሰራም አስረድተዋል . ።

በነስሩ ባደዢ

Share this Post