የክልልና የህዝብ ተወካዮች ምክርቤት አባላት በሆሳዐና ከተማ የልማትና መልካም አስተዳደር ችግሮች ለመፍታት በተከናወኑ ተግባራት ዙርያ ከከተማው የአመራር አካላትጋር ተወያይተዋል ።

የክልልና የህዝብ ተወካዮች ምክርቤት አባላት በሆሳዐና ከተማ የልማትና መልካም አስተዳደር ችግሮች ለመፍታት በተከናወኑ ተግባራት ዙርያ ከከተማው የአመራር አካላትጋር ተወያይተዋል ።

የከተማው መንግስት ኮሙኒኬሽን ጉዳዮች ጽ/ቤት ነሐሴ 14/2014ዓ.ም

በውይይቱ ላይ የፌዴራል ፣ የክልል ተወካዮች ም/ቤት አባላት ፣ የዞንና የከተማው አመራሮች እንዲሁም የከተማው ምክርቤት ቋሚ ኮሚቴ አባላት ተሳታፊ ሆነዋል ።

በከተማው በመሬት አስተዳደር ፣በአገልግሎት አሠጣጥ ፣በገቢ አሰባሰብ ፣በመሠረተ -ልማት፣በትምህርት ጥራት ፣በህገ-ወጥ ንግድ ፣በትራንስፖርትና በሌሎች ዘርፎች በሚታዩ ችግሮች ዙርያ ለተነሱ ጥያቄዎች በሚመለከታቸው የካቤኔ አካላት ማብራሪያና ምላሽ ተሰጥቷል ።

በተጨማሪም በከተማው መሰረተ-ልማቶች የማስፋፋት ሥራዎች ተከትሎ የማብራትና የውሃ አገልግሎቶችን ተደራሽ ለማድረግ ቅንጅታዊ አሠራር አለመኖርን በቀጣይ ሊስተካከል እንደሚገባም በውይይቱ ላይ ተጠቁሟል።

Share this Post