የሀዲያ ዞን ሴቶች አሸባሪው ህወሐት የቀረበለትን የሠላም አማራጭ ወደ ጎን በመተው የከፈተውን ጦርነት በማውገዝ በሆሳዕና ከተማ ሠላማዊ ሠልፍ አካሄዱ
ነሐሴ 24/2014 ዓ.ም (የሀዲያ ዞን መ/ኮ/ጉ/መምሪያ)
ንጹሃንን እየጨፈጨፈ ያለውን ይህን የኢትዮጵያና የትግራይ ህዝብ ዕዳ የሆነ ቡድን ከህዝብ ጫንቃ ላይ ለማውረድ ከመንግሥት ጎን በመሆን ድጋፍ እንደሚያደርጉ የዞኑ ሴቶች ገልፀዋል።
ሴቶቹ ህወሃት ሀገር በመራባቸው ዓመታት በስውር ይገድልና ያፈናቅል የነበረውን ተግባር በይፋ የኢትዮጵያ መከላከያን በመጨፍጨፍ የኢትዮጵያ ጠላት መሆኑን በግልጽ ማሳየቱን ተናግረዋል።
ሴቶች ጦርነትን አጥብቀው የሚቃወሙና የሚጠሉ ቢሆንም ንጹሃንን እየጨፈጨፈ ያለውን ይህን የኢትዮጵያና የትግራይ ህዝብ ዕዳ የሆነ ቡድን ከህዝብ ጫንቃ ላይ ለማውረድ ከመንግሥት ጎን በመሆን ድጋፍ እንደሚያደርጉ ገልፀዋል።
ሁሉም ዜጋ አካባቢውን ነቅቶ እንዲጠብቅ ጥሪ ያቀረቡት ሴቶቹ ዜጎች እንዲፈናቀሉና የህዝብ ሰላምና ደህንነት አደጋ የሆነ ቡድን በንጹሃን ላይ ተጨማሪ ዕልቂት እንዳይፈጽም መንግስት የማያዳግም እርምጃ እንዲወሰድ ጥሪ አቅርበዋል።
ጦርነት አስከፊ ነው በተለይ ጉዳቱ ህፃናትና እናቶች ላይ የሚያደርሰው ጥፋት ከፍተኛ መሆኑን የተናገሩት የሀዲያ ዞን ረዳት የመንግሥት ተጠሪ አቶ ከይረዲን ራመቶ።
አሸባሪው ቡድን መቀሌ መሽጎ የትግራይ ህዝብ ከሌላው የኢትዮጵያ ህዝብ ለመነጠል እየሰራ መሆኑን በመግለፅ
የሀገር ሽማግሌዎች ፣ የሀይማኖት አባቶች ፣ እናቶችና የተለያዩ ታዋቂ ግለሠቦች ለሠላም ያደረጉትን ጥረት ረግጦ ለትግራይ ህዝብን በሠላሙና በልማቱ ሲደግፍ የኖረውን የሀገር መከላከያ ላይ ተኩስ ከፍቶ በመጨፍጨፍ በሀገርና በህዝብ ክህደት የፈፀመ አረመኔ ቡድን መሆኑን ተናግረዋል።
የሀገራችን የፖለቲካ ችግር መፍትሄ የሠላም አማራጭ ብቻ መሆኑንና መንግስትም ዛሬም ፣ነገም ችግሩን ለመፍታት ዝግጁ መሆኑን ተናግረዋል።
ሀገር ተገዶ የገባውን ጦርነት ለመቀልበስ እናቶችና አባቶች እንደወትሮው ለሀገር መከላከያ ሰራዊት የስንቅ ድጋፍ እንዲያደርጉ ወጣቶች ደግሞ ወደ ግንባር እንዲዘምቱ ጥሪ አቅርበዋል።
የሀዲያ ዞን ብልጽግና ፖርቲ ሴቶች ሊግ ምክትል ሀላፊ ወ/ሮ ወጋሜ ጴጥሮስ በበኩላቸው አሸባሪው ህወሐት ከጅምሩ ለውጡ እንዳይሳካና እንዲደናቀፍ የተለያዩ መሰናክሎችን ሲፈጥር መቆየቱን አስታውሰው።
የተዘረጉ የሠላም እጆችን በመርገጥ የተለያዩ ጽንፈኛ አክራሪ ሀይሎችን በማደራጀት በመላው ሀገሪቱ ህይወት እንዲጠፋ ንብረት እዲወድም የተቀናጀ የኢኮኖሚ አሻጥር በመፈፀም የሀገሪቱን ኢኮኖሚ የማሽመድመድ ተግባር መፈፀሙን ተናግረዋል።
መንግስት ለትግራይ ህዝብ የሠላም እጁን ቢዘረጋም ያለጦርነት መኖር የማይችለው አሸባሪው የህውሐት ቡድን ዳግም የደሃ የትግራይ እናቶችን ልጆች በመማገድ በንፁሃን ላይ ጥቃት እየፈጸመ ይገኛል።
ይህን መላው ኢትዮጵያዊያን በመረዳት ይህን እኩይ ቡድን ከኢትዮጵያ ጫንቃ ላይ አሽቀንጥሮ ለመጣል በሚደረገው ዘመቻ ሁሉም የበኩሉን ሚና እንዲጫወት ጥሪ አቅርበዋል።
በኤልያስ ቲርካሶ