በውይይት መድረኩ የዞን፣ የሆሳዕና ከተማ አስተዳደርና የሌሞ ወረዳ ፖሊስ አመራሮች እንዲሁም የህብረተሰብ ተወካዮችና የሀይማኖት አባቶች ተሳትፈዋል።
በምክክሩ የተሳተፉ አንዳንድ የህብረተሰብ ተወካዮች በሰጡት አስተያየት በአሁን ወቅት የፀጥታ መዋቅር ከዚህ ቀደም ከነበረው በየመንደሩ ተደረሽ እየሆነ በመምጠቱ በቅርበት የከተማው ጸጥታና ደህንነት ለማስጠበቅ ያግዛል ነው ያሉት።
የከተማው አሁናዊ ሁኔታ የፀጥታ መሻሸሎች ቢኖሩም በከተማዋ ለህብረተሰቡ ሥጋት የሆኑ ህገ ወጥ እንቅስቃሴዎች ላይ የጸጥታው መዋቅር ጥብቅ ቁጥጥርና ክትትል ሊደረግበት ይገባል ሲሉ በውይይቱ የተሳተፉ የህብረተሰብ ተወካዮች ተናግረዋል።
በተለይም ህጋ-ወጥ መሣሪያ የታጠቁ ሰዎች በከተማዋ እየተባረከቱ በመምጣታቸው ለህብረተሰቡ ሥጋት መሆናቸውን አንስተው ተገቢው ቁጥጥር ሊደረግበት እንደሚገባ አመላክተዋል።
የዞኑ ፖሊስ መምሪያ የወንጃል መከላከል ዲቨዠን ኃላፊ ኮ/ር ሳይሉ ኃይሌ በዚህ ወቅት እንዳሉት÷ በከተማው በ6ቱም ቀበሌና በ1መቶ 62 መንደሮች መኖሩን ጠቅሰው በእዚህ አካባቢዎች የሚፈጠሩ ወንጀሎች ሁለንተናዊ ቁጥጥር በማድረግ ከህብረተሰቡ ጋር ውይይት በመፍጠር እያንደንዱ ግለሰብ የራሱን መንደር በተደረጀ መንገድ ጥበቃ እንዲያደርግ ይሠራል ብለዋል።
ህብረተሰቡ በሠላም ወጥተው እንዲገባ እና ከወንጀል የፀደች ከተማ ለማድረግ በከተማው የአካራይ ተካራይ ልየተ፤ አልጋ ቤቶች ላይ ሥር ነቀል ፍተሻ በማድረግ እና በመንገድ ደር የሚከናወኑ ህገ-ወጥ ንግዶች ቁጥጥር ይደረጋል ሲሉ ገልፀዋል።
ይህን ውጤታማ ለማድረግ የከተማ ማህበረሰብ ከፀጥታ መዋቅር ጋር መረጃ በመሥጠትና ወንጀለኞቹን በመጋለጥ ትብብር እንዲያድርጉ ጠይቀዋል።
በዚህም ህብረተሰቡ የነቃ ተሳትፎ በማድረግ አካባቢውን በራሱ እንዲጠብቅና ከወንጀል ሥጋት ነፃ የሆነች ከተማ መፍጠር ይገባል ነው ያሉት።
በተያዘው ዓመት ሌሎች ዞኖች ከዞናችን የሰላምና ፀጥታ ተሞክሮ እንዲማሩ እንደሚሠራም አያይዞ ተናግረዋል።
የሀዲያ ዞን ሰላምና ፀጥታ መምሪያ ኃላፊ አቶ አረጋ መዴቦ በበኩላቸው በዞኑ ሁሉ አቀፍ ሰላም እንዲሰፍን በማስቻል ሆሳዕና ከተማ ከወንጀል የፀደች ከተማ እናደርጋታለን ብለዋል።
ይህ እንዲሆን ለማስቻል በሰላምና ፀጥታ ዙሪያ፣ ስጋቶችን በመለየትና ለህብረተሰቡ ግንዛቤ በመፍጠር የተቀናጀ ሥራ እንደሚሰራም አብራርተዋል።
ህብረተሰቡ የከተማውን ገጽታ ለመጥልሻት ከተለያዩ አካላት የሚሠረጩ የሀሰተኛ መረጃ እንዳይታላል ጥንቃቄ ማድረግ እንሚገባ አሳስባዋል።
በደገለ ባምቦሬ