ኢትዮ ቴሌኮም በሀዲያ ዞን ሆሳዕና ከተማ ያስገነባው የዲጂታል መማሪያ ማዕከል ተመረቀ

ኢትዮ ቴሌኮም በሀዲያ ዞን ሆሳዕና ከተማ ያስገነባው የዲጂታል መማሪያ ማዕከል ተመረቀ

**************

(ኢ ፕ ድ)

ኢትዮ ቴሌኮም በሀዲያ ዞን ሆሳዕና ከተማ አስተዳደር ሄጦ አጠቃላይ 2ኛ ደረጃ ትምህርት ቤት ያስገነባው የዲጂታል መማሪያ ማዕከል ተመርቆ አገልግሎት መስጠት ጀምሯል።

ማዕከሉ 21 ኮምፒውተሮች ከ10 ሜጋ ባይት ፈጣን የኢንተርኔት አገልግሎት፣ ኮፒና ፕሪንተር ማሽኖች ተሟልቶ ለተማሪዎች በቂ አገልግሎት እንዲሰጥ መደራጀቱ ተገልጿል።

የዲጅታል መማሪያ ማዕከልን ለሁሉም ተደራሽ ለማድረግ እንደሚሰራ የሀዲያ ዞን ዋና አስተዳደሪ አቶ አብርሃም መጫ ተናግረዋል። ኢትዮ ቴሌኮም በአጭር ጊዜ ውስጥ ለአገልግሎት በማቅረቡ ሊመሰገን ይገባል ብለዋል ዋና አስተዳዳሪው።

የደቡብ ክልል ትምህርት ቢሮ ምክትል ኃላፊ አቶ ስንታየሁ ስምኦን፣ የመማር ማስተማር ስርዓቱ ፈጣንና በወቅቱ ተደራሽ ለማድረግ የዲጂታል መማሪያ ማዕከላት ሚና ከፍተኛ ነው። ይህን ለማስፋፋትና ለማጠናከር ክልሉ አስፈላጊውን ሁሉ ድጋፍ እንደሚያደርግ ተናግረዋል።

የደቡብ ደቡብ ምዕራብ ሪጅን ኢትዮ ቴሌኮም ዳይሬክተር አቶ ሹሜ አብሽሮ ዲጂታል ዓለምን ዕውን ለማድረግ ኢትዮ ቴሌኮም ከ44 ሚሊዮን ብር በላይ በጀት በመመደብ በሀገር አቀፍ ደረጃ 140 ሺህ 96 ተማሪዎች ተጠቃሚ የሚያደርጉ የዲጂታል መማሪያ ማዕከላት በ66 ትምህርት ቤቶች ላይ ገንብቶ የሙከራ ትግበራ መጀመሩን ገልጸው በሆሳዕና ከተማ የሄጦ አጠቃላይ 2ኛ ደረጃ ትምህርት ቤት የዚህ ዕድል ተጠቃሚ መሆኑን ተናግረዋል።

ተማሪዎች ከዲጂታል ዓለም ጋር በመተዋወቅ ለፈጠራና ችግር ፈች ዕውቀት በማግኘት ውጤታማ ስራ እንዲሰሩ ይህ ተግባር በቀጣይ ተጠናክሮ እንደሚሰራ ጠቁመዋል።

የሀዲያ ዞን ትምህርት መምሪያ ሀላፊ ዶክተር አበበ ሎላሞ በበኩላቸው ተማሪዎች በሀገር አቀፍና አለም አቀፍ ተወዳዳሪ ለማድረግ ቴክኖሎጂ አንዱ መሆኑን ገልፀው። ዲጂታል መማሪያ ማዕከሉ በትምህርት ጥራት ላይ ለሚሰራው ስራ ያለው ፋይዳ ከፍተኛ መሆኑን መናገራቸውን የሀዲያ ዞን ኮሙኒኬሽን ጉዳዮች መምሪያ መረጃ ያመለክታል።

ኢትዮጵያን እናልማ፣ እንገንባ፣ እንዘጋጅ‼️

ሀገርን በዘላቂነት እናልማ‼️

የፈረሰውን አብልጠን እንገንባ‼️

ለማንኛውም ፈተና እንዘጋጅ‼️

ተጨማሪ የመረጃ አማራጮቻችን ‼️

Share this Post