"ያሆዴ" ፌስቲቫል እና ባዛር በይፋ ተከፈተ

የሀዲያ ብሔር ዘመን መለወጫ "ያሆዴ" በዓልን ምክንያት በማድረግ በሆሳዕና ከተማ የተዘጋጀው ታላቅ ፌስቲቫል እና ባዛር በይፋ ተከፈተ።

የሀዲያ ዞን ዋና አስተዳዳሪ አቶ አብርሃም መጫ፣ የዞኑ ዋና የመንግስት ተጠሪ አቶ ጌታቸው ሌሊሾ እና የሆሳዕና ከተማ አስተዳደር ከፍተኛ የመንግስት የስራ ኃላፊዎች በተገኙበት በይፋ ተከፍቶ ጉብኝት ተደርጓል።

እስከ በዓሉ የዋዜማ መዳረሻ የባህል ኤግዝቢሽን፣ ያሆዴ የጎዳና ላይ እሩጫ እና የተለያዩ ዝግጅቶች ይካሄዳሉ።

የ"ያሆዴ" በዓል ዋዜማ (በአተካን ሂዕሞ) በአተካና ምሽት ይደምቃል። በዕለቱም የአባቶች ምርቃት፣ የሳቴና የጋቢማ ስርዓት ይከወናል።

"ያሆዴ" ወንዶች በያሆዴ፣ ሴቶች በሂቦንጎ ጭፈራ ያደምቁታል። የሴቶች የቁንጅና ውድድርና ባህላዊ አለባበስና አጋጌጥ ለበዓሉ አከባበር ልዩ ድባብ ያላብሱታል።

ኑ "ያሆዴን" በአንድ ላይ ተሰባስበን ሆሳዕና ከተማ በሚገኘው የበዓሉ ማክበሪያ ስፍራ "ሀዲይ ነፈራ" መስከረም 14 ቀን በጋራ እናክብር። ሁላችሁም ተጋብዛችኋል።

Share this Post