22
Sep
2022
መስከረም 11/2015 ዓ.ም (የሀዲያ ዞን መ/ኮ/ጉ/መምሪያ)
የሀዲያ የዘመን መለወጫ ያሆዴ በዓልን አስመልክቶ ለአንድ መቶ ዘማች ቤተሰብ 3 መቶ ሺህ ብር የሚያወጣ የምግብና የትምህርት ቁሳቁስ ድጋፍ ተደረገ።
ድጋፉ በዞኑ አስተዳደር፣በሴቶችና ሕፃናት እንዲሁም በሚሊሻ ጽ/ቤት ትብብር የተዘጋጀ ነዉ ተብሏል።
ድጋፉን ያበረከቱት የሀዲያ ዞን ዋና አስተዳዳሪ አቶ አብርሃም መጫ ቤተሰብ እንዲኖር ሀገር መኖር አለበት የሀገርን ህልውና ጠብቆ ለማቆየት ወደ ግምባር የዘመቱ ወገኖችን ቤተሰቦቻቸውን ማገዝ ተገቢ ነዉ ብለዋል።
ዋና አስተዳዳሪዉ አክለዉ ይህን መልካም ሀሳብ ያሰቡትንና ተግባራዊ እንዲሆን ያስተባበሩ አካላት አመስግነዋል።
በጠቅላላው ለዘማች ቤተሰቦቹ 500 ኩንታል በቆሎ 100 ደርዘን ደብተርና 20 ፓኬት እስክርብቶ የተበረከተላቸው ሲሆን ይህም ወደ ገንዘብ ሲተመን 300 ሺህ ብር እንደሚያወጣ ተጠቁሟል።
በድጋፍ ለእያንዳንዳቸው የዘማች ቤተሰቦች 50 ኪሎ ግራም በቆሎ 1 ደርዘን ደብተርና 8 እስክርብቶ ተበርክቷል።
በአልያስ ተሰማ