የሀዲያ ዞን ኢንቨስትመንት ጽ/ቤት ኃላፊ አቶ እዮብ ጩፋሞ
ለ2015 ዓ.ም የሀዲያ ዘመን መለወጫ "ያሆዴ" በዓል የእንኳን አደረሳችሁ መልዕክት አስተላልፈዋል።
የሀዲያ የዘመን መለወጫ "ያሆዴ" በዓል የማህበረሰቡን ባህልና እሴት ለዘመናት ይዞ የቆየ የመልካም ምኞት መግለጫ በዓል መሆኑን በመግለፅ።
በኢንቨስትመንት ዘርፍ በገጠር በከተማ የቴክኖሎጂ ሽግግርን በማሳለጥ የተለያዩ ልማቶች በስፋት እየተሰሩ መሆኑን አቶ ኢዮብ ጠቁመዋል።
የዞኑ የአካባቢ ጥበቃና ደን ልማት መምሪያ ኃላፊ አቶ ደሳለኝ ሱራጅ በዓሉን ሲናከብር ሁሉም ህብረተሰብ ክፍል አካባቢውን በመፅዳትና በክረምት ወቅት የተተከሉ የተለያዩ ችግኞች በማንካበከብ በዓሉን እንዲያሰልፉ አሳሰበዋል።
የሀዲያ ዞን ሚሊሻ ጽ/ቤት ኃላፊ አቶ ወንድሙ አኒሴ "ያሆዴ" በዓል በሀዲያ ብሔር አሮጌ ዓመት ሸኝቶ አድሱን ዓመት የሚጀምርበት በመሆኑ በርካታ ፋይዳዎች መኖሩን ገልጿል።
በዓሉን ስናከብር የአካባቢያችንን ብሎም የአገራችንን ሰላምና ደህንነትን በጋራ በመጠበቅ ለሠላም ዘብ ልንቆም ይገባል ብለዋል በመልዕክታቸው፡፡
የሀድያ ዞን ህብረት ሥራ ልማት ጽ/ ቤት ኃለፊ አቶ ዘሪሁን ዋጄቦ እንደተናገሩት በበዓሉ ምክንያት ሸማቾች ህ/ሥራ ማህበራት ገቢያ በመረጋጋት ጉልህ ሚና ስላለው በፊጆታ ዕቃ ላይ ዋጋ ሳይጫምሩ ህብረተሰብን እንዲያገለግሉ አሳስበዋል።
"ለያሆዴ" በዓል በሀገርና በውጭ ለሚኖሩ የሀዲያ ተወላጆችና ለመላው ኢትዮጵያውያን በሙሉ የእንኳን አደረሳችሁ መመልዕክት አስተላልፈዋል።