የከተማ ልማትና ኮንስትራክሽን የኢንተርፕራይዝና ኢንዱስትሪ የሠራተኛና ማህበራዊ ጉዳይ መምሪያዎች ለያሆዴ በዓል እንኳን አደረሳችሁ መልዕክት አስተላለፉ

የሀዲያ ዞን የኢንተርፕራይዝና ኢንዱስትሪ ልማት መምሪያ ኃላፊ አቶ ጸጋው ሙልጌታ የከተማ ልማትና ኮንስትራክሽን መምሪያ ኃላፊ አቶ ዳንኤል መኮሮ የሠራተኛና ማህበራዊ ጉዳይ መምሪያ ኃላፊ አቶ አዲሴ አውቶ ያሆዴ በዓልን በማስመልከት እንኳን አደረሳችሁ መልዕክት አስተላልፈዋል።

የተከበራችሁ የሀዲያ ተወላጆችና ወዳጆች እንዲሁም መላው ኢትዮጵያዊያን እንኳን ለ2015 ዓ.ም ለሀድያ ዘመን መለወጫ ያሆዴ በዓል በሰላም አደረሳችሁ፣አደረሰን!!

የያሆዴ በዓል በብሔሩ ተወላጆች ዘንድ ትልቅ ቦታ የሚሰጠዉ በዓል ነው። ለዚህም በብሔሩ ባህል መሠረት አባቶች፣ እናቶችና ልጆች የየራሳቸዉን ዝግጅት በማድረግ በጉጉት የሚጠብቁት ትልቅ በዓል ስለመሆኑም ገልፀዋል

በዓሉን ስናከብር የተቸገሩትን በመርዳት፣ የአካባቢያችንን ብሎም የአገራችንን ሰላምና ደህንነትን በጋራ በመጠበቅ ሊሆን ይገባል ብለዋል በመልዕክታቸው፡፡

በዓሉ የሠላም፣ የይቅርታ፣የአንድነትና የብልጽግና እንዲሆን መልካም ምኞታችን ገልጸዋል።

በኤልያስ ተሰማ

Share this Post