11
Oct
2022
የከተማው የመንግስት ኮሙኒኬሽን ጽ/ቤት ጥቅምት01/2015 ዓ.ም
የከተማው ትራንስፖርት ጽ/ቤት ኃላፊ አቶ ግዛቸው ጋዶሬ ዛሬ የሠላም የባጃጅ ታክሲ ባለንብረቶች ማህበር ጉባኤ በንግግር ሲከፍቱ እንደገለፁት ማህበራቱ በሚያካሄዱት ጉባኤ የ2014 ዓ.ም የዕቅድ ክንውን አፈፃፀም እንዲሁም የኦዲት ሪፖርት ቀርቦ ውይይት ይደረጋል ።
በተጨማሪም የ2015 ዓ.ም ዕቅድ ቀርቦ ውይይት የሚደረግበት ሲሆን በቀጣይ ሦስት ተከታታይ ቀናት ብርሃን፣ፍቅርና አንድነት የባጃጅ ታክሲ ባለንብረቶች ማህበራት በተመሳሳይ ሁኔታ ጉባኤያቸውን እንደሚያካሂዱ ኃላፊው ጠቁመዋል ።
አክለውም በትራንስፖርት ዘርፍ ለትራፊክ አደጋ መንስኤ የሚሆኑ ችግሮች ለመፍታት ከባለድርሻ አካላት ጋር በመተባበር ትኩረት ተሰጥቶ እየተሠራ መሆኑንም አስረድተዋል ።
በመጨረሻም በህገ-ወጥ ባለሶስት እግር ተሽከርካሪና ከታሪፍ በለይ በሚያስከፍሉ አሽከርካሪዎች ላይ እርምጃ እንደምወሰድና የታለመለትን የነዳጅ ድጎማ ታጠቃሚ እንዲሆኑ ኃላፊው መልዕክት አስተላልፈዋል ።