13
Oct
2022
የከተማው የመንግስት ኮሙኒኬሽን ጽ/ቤት ጥቅምት01/2015 ዓ.ም
አረጋውያንና የሚመለከታቸው ባለድርሻ አካላት በዓሉ ሲከበር በዓለም አቀፍ ደረጃ ለ31ኛ በሀገራችን ለ30ኛ ጊዜ መሆኑን የተገለፀ ሲሆን ለአረጋውያን የተደረጉ የድጋፍ ና እንክብካቤ ተግባራት ሪፖርት ቀርቦ ውይይት ተደርጎበታል ።
የጽ/ቤቱ ኃላፊ አቶ ተስፋዬ ቲርካሶ እንደገለጹት በከተማው ባለፋት ሦስት ወራት ለ1,543 አረጋዊውንና አቅመ ደካሞች ከ6 ነጥብ 6 ሚሊየን ብር በላይ ግምት ያለው የዓይነትና የገንዘብ ድጋፍ ተደርጓል ።
የሆሳዕና ከተማ የመንግስት ዋና ተጠሪ አቶ ሳሙኤል ታደሰ በበኩላቸው የዓረጋውያን ቀን ስናከብር ለአረጋውያን ክብር በመስጠትና የሀገር ባለውለታ መሆናቸውን በመገንዘብ የሚደረግላቸውን ሁለተናዊ ድጋፍ ተጠናክሮ ሊቀጥል እንደሚገባም አሳስበዋል ።