የሆሳዕና ከተማ አስተዳደር ፑል አመራሮች በነበራዊ ጉዳዮች እና ከአዲሱ ሥራ አስፈፃሚ አመራር አካላት ጋር የትውውቅ መድረክ ተካሄደ ።

የሆሳዕና ከተማ አስተዳደር መንግስት ኮሙኒኬሽን ጉዳዮች ጽ/ቤት ጥቅምት 8/2015 ዓ.ም

የሆሳዕና ከተማ አስተዳደር ከንቲባ አቶ ሊሩ ጀማልና የከተማው የመንግስት ዋና ተጠሪ ዶ/ር ደበበ ገብሬ በየበኩላቸው እንደገለፁት በርካታ የስራ ፈተናዎች እና መፍትሔዉም በጋራ በመሆን የምንፈልግበትና ከተማችንን ዉብ ፅዱና ማራኪ በማድረግ ለነዋሪዎቿ ምቹ ለማድረግ የተጀመረዉን ጥረት ለማገዝ እድል በማግኘታቸዉ መደሰታቸዉን ገልፀዋል።

ኃላፊዎቹ አክለዉም በተለይ ከተማዉ የሚተዳደረዉ በዉስጥ ገቢ በመሆኑ በፀጥታ ፣ በገቢ አሰባሰብ ፣ በንግድ እና በከተማው እየተሠራ በሚገኙ መጠነ ሰፍ መሠረተ ልማት ዙርያ ትኩረት በመስጠት ልሠራ እንደሚገባ ጠቁመዋል።

Share this Post