04
Nov
2022
የሆሳዕና ከተማ ከንቲባ አቶ ሊሬ ጀማል በከተማው በየካቲት 25/67 2ኛ ደረጃ ት/ቤት በተካሄደው የአከባበር ሰነ-ስርዓት ላይ እንደገለጹት ዕለተ ሰኞ ጥቅምት 23/2013 ዓ.ም ለጥቅምት 24 አጥቢያ የኢፌዲሪ መከላከያ ሰራዊት ሰሜን እዝ አባላት ሽበርተኛው ሕወሀት በክህደት ጥቃት መፈጸሙ ሁሌ የሚታወስና ፈፅሞ የማይዘነጋ ነው ።
አክለውም የዛሬውን የመታሰቢያ በዓል ኢትዮጵያ ባሸነፈችበትና የህወሐት አሸባሪ ሀይል በተሸነፈበት ማግስት የሚከበር በመሆኑ ልዩ እንደሚያደርገውም ከንቲባው ጠቁመዋል ።
የከተማው ት/ጽ/ቤት ኃላፊ አቶ አዳነ ዘመድኩን በበኩላቸው ህብረተሰቡ በተሠማራበት ሁሉ ውጤት በማስመዝገብ ሀገር ለመበተን ጥቃት የፈጸሙብንን ህወሀትንና ጀሌዎቹን በመመከት የሀገራችንን ሉአላዊነት ለማስጠበቅ መስዋእት እየከፈለ ካለው ጀግናው የመከላከያ ሰራዊታችን ጎን ደጀን በመሆን እያደረገ የለውን ድጋፍ በቀጣይነት ሊያረጋግጥ እንደሚገባም ተናግረዋል ።
በፕሮግራሙ ላይ የት/ቤቱ ተማሪዎች የመከላከያ ሠራዊታችን ጀግንነት የሚገልጹ ግጥሞችና ድራማዎች በማቅረቡ በዓሉን
አድምቀዋል።
"ጥቅምት 24ን መቼም አንረሳውም"!!!