በምሻ ወረዳ በኩታ ገጠም የለማ የስንዴ ማሳ የመስክ ምልከታ ተደረገ

በሀዲያ ዞን በምሻ ወረዳ ሞርሲጦ ከተማ በ14 ሄክታር መሬት ላይ በክላስተር ግብርና የለማ ኩታ ገጠም የስንዴ ማሳ የመስክ ምልከታ ተደርጓል።

የማሳዉ ባለቤት አቶ አብርሃም ቶቤ እንደተናገሩት ከማሳ ዝግጅት እስከአሁን ጥሩ ምርት ለማግኘት የተከደበትን ሂደት አብራርተዉ በአሁን ወቅት ጥሩ ምርት እንደሚጠብቁ እና የባለሙያ እገዛ ተጠናክሮ መቀጠል እንዳለበት አሳስበዋል።

የወረዳዉ እርሻና ተፈጥሮ ሀብት ልማት ጽ/ቤት ኃላፊ አቶ አለማየሁ ኤርደዶ በበኩላቸዉ እየተደረገ ያለዉ ሙያዊ ድጋፍና ክትትል ተጠናክሮ እንደሚቀጥ ተናግረዋል።

በመስክ ምልከታውም የክልል፣ የዞን፣ የወረዳና የከተማ አስተዳደር ከፍተኛ አመራሮችና የመንግስት የስራ ኃላፊዎች ተገኝተዋል።

ምንጭ:- የም/ወ/መ/ኮ/ጉ/ጽቤት

Share this Post