በሆሳዕና ከተማ የሚገኙ ወጣቶች ከከተማውና ቀበሌያት አመራር አካላት ጋር በመሆን በአራዳና በልች አምባ ቀበሌ " ቆሻሻን የሚፀየፍ ማህበረሰብን መፍጠር " በሚል መሪ ቃል የጽዳት ዘመቻ አካሄደዋል ።

የሆሳዕና ከተማ አስተዳደር መንግስት ኮሙኒኬሽን ጉዳዮች ጽ/ቤት

ህዳር 7/2015 ዓ.ም

በጽዳት ዘመቻ ፕሮግራሙ ላይ የከተማዉ ፣ የቀበሌው አመራር አካላት እና የሁሉም ቀበሌ ወጣቶች ሊጎችን ጨምሮ ተሳታፊ ሆነዋል ።

የሆሳዕና ከተማ አስተዳደር የመንግስት ዋና ተጠሪ ዶ/ር ደበበ ገብሬ እንደገለፁት በከተማችን በሚካሄደው ዘርፍ ብዙ ተግባራት ላይ የሁሉም ማህበረሰብ ከፍሎች በቀጣይነት የበኩላቸውን ኃላፊነት ሊወጡ እንደሚገባም ጠቁመዋል ።

አክለውም በሚሠሩ መሠረተ ልማቶችና በጽዳት ዘመቻ ላይ በንቃት በመሳተፍ ከተማውን በማስዋብ የገጸ-በርከት ተቆዳሽ ለመሆን ተጠናክሮ መሥራት እንደሚገባ አሳስበዋል ።

በመጨረሻም በሁሉም ቀበሌያት የሚገኙ ወጣቶችና ሌሎችም ባለድርሻ አካላት

በጊዜው የጽዳት ሥራንና ሌሎችንም ተግባራት እየሰሩ የቆዩ መሆኑን አስታዉሰዉ ይህንኑ ተግባራ በማስቀጠል "ቆሻሻን የሚፀየፍ ትውልድን መፍጠር "በሚል መሪ ቃል የከተማው ማህበረሰብ ከወጣቶቹ ጎን በመቆም ከማኖር ጋር አቀናጅተዉ እንዲከዉኑ ጥሪ አቅርበዋል ።

Share this Post