05
Sep
2025
"ኢትዮጵያን ወደ ተምሳሌት ሀገር !" በሚል መሪ ቃል ለሁለት ተከታታይ ቀናት ለብልፅግና ፓርቲ አባላት ሲሰጥ የነበረውን ስልጠና አጠናቀን እየተሠሩ ያሉ የልማት ስራዎችን ጉብኝት ማድረጋችን ከተማችንን በሁሉም የልማት ዘርፎች ተምሳሌት እንድትሆን ለማድረግ በትኩረት እንድንሰራ ቁጭትና መነሳሳትን እንደፈጠረባቸውም ገልጸዋል ።
አሁን በከተማዉ እየተገነቡ ያሉ የልማት ስራዎች በአጭር ጊዜ በማጠናቀቅ ለአገልግሎት በማብቃት ከፊታችን የሚከበረዉን "ያሆዴ"እና የኢትዮጵያ ብሔር ብሔረሰቦች ባዓል በደማቅ ሁኔታ ለማክበር ዝግጂት እየተደረገ እደሆነ አቶ ደሳለኝ ገልፀዉ የተጀመረውን ከተማን የማስዋብ ስራ ሁሉም ባለድርሻ አካላት አጠነክረው መቀጠል እንደሚገባም አሳስበዋል ።
አንዳንድ ባለሙያዎች በዕለቱ በጉብኚት ቦታ በሰጡት አስተያየት በከተማው እየተሠራ ያሉ የልማት ስራዎች ተስፋ ሰጪ መሆኑን ተናግረው በመስክ ምልከታ ባዩት የልማት ስራዎች ደስተኛ መሆናቸውንም ገልፀዋል ።