የሆሳዕና ከተማ አስተዳደር አመራሮች የአመራር ስልጠና መድረክ ካጠናቀቁ በኋላ በከተማው እየተሠራ ያሉ የልማት ስራዎችን ተዘዋውረው ጉብኝት አድርገዋል ።

ከንቲባ ደዊት አክለውም ዛሬ ምልከታ ያደረግነው የኮሪደር ልማት ስራዎች የእስማርት ሲቲ ደረጃን የጠበቁ የእግረኞች ፣የአካል ጉዳተኞችና የሳይክል መንገዶችን ያካተተ በመሆኑ ከዚህ ቀደም በተሽከርካሪ ሲደርስ የነበረውን አደጋ በከፍተኛ ሁኔታ ይቀንሳል ብለዋል ።

እየተተከለ ያለ እስማርት የመብራት ፖል ብርሃን ከመስጠት ባለፈ የተለያየ አገልግሎት እንዳለውም ገልፀው የአቢዮ ኤርሳሞ መታሰቢያ እስታዲየም ደረጃ የማሻሻል ግንባታን ጨምሮ ሌሎችም በተያዘላቸው ጊዜ ለማጠናቀቅ በልዩ ትኩረት እንደሚሰራም ገልፀዋል ።

የሆሳዕና ከተማ ማዘጋጃ ቤት ስራ አስካጅ አቶ ደሳለኝ ደፋር በበኩላቸው የኮሪደር ልማትን ጨምሮ በከታማችን እየተሠሩ ያሉ ሌሎች የልማት ስራዎችም የስራ ባህላችንን የቀየረና የይቻላል መንፈስን በውስጣችን ፈጥሮዋል በማለት ተናግረዋል ።

በከተማችን የልማት ፍላጎት በጣም ሰፊ ነዉ ያሉት አቶ ደሳለኝ በቀጣይ የከተማው አቅም በሚፈቅደው ሁሉ በሁሉም አቅጣጫ ልማቱን ተደራሽ ለማድረግ ከዚህ በበለጠ ለህዝባችን እሰከ ታች ወርደን በጋራ እንሰራለን በማለት አስተያየታቸውን ሰጥተዋል ።

በመስክ ምልከታ ወቅት ያነጋገርናቸው አንዳንድ አመራሮች በጋራ በሰጡት አስተያየት በከተማው እየተሠራ ያሉ የልማት ስራዎች ለከተማው ትልቅ ተስፋ ሰጪ መሆኑን አንስተው ማንኛውንም የልማት ስራ ህዝብና መንግስት ተቀራርቦ ከሰራ ተግባራዊ መድረግ ይቻላል ብለው በመስክ ምልከታ ባዩት የልማት ስራዎች በጣም ደስተኛ መሆናቸውን ገልፀዋል ።

የምስጋኑ ዎሜ ጠቅለል ተቋራጭ እና ምህረቱ መለሰ ጠቅላላ ተቋራጭ ባለቤቶች በጋራ በሰጡት አስተያየት የኮሪደር ልማትን ጨምሮ ሌሎች ግንባታዎችንም በተያዘላቸው ጊዜ ለማጠናቀቅ ሌት ቀን በትኩረት እየሠሩ እንደሆናም ተናግረዋል ።

በመጨረሻም በዕለቱም የከተማ ስራ አስፈፃሚዎችን ጨምሮ የዞን፣የከተማና የሁሉም ቀበሌ አመራሮች በመስክ ምልከታው ተገኚተዋል።

በጌታቸው ደስታ

 

Share this Post