በሆሳዕና ከተማ አስተዳደር ከአገልግሎት አሰጣጥ ጋር የተያያዙ የመልካም አስተዳደር ችግሮች ለመፍታት አመራሩ በቁርጠኝነትና በተጠያቂነት መንፈስ ሊሰራ እንደሚገባ ተገለፀ ።

በከተማው የተለዩ የመልካም አስተዳደር ችግሮችንና ችግሮቹ ለመፍታት እየተደረጉ ያሉ ጥረቶችን በሰነዱ የተዳሰሰ ሲሆን በተለይም ከአገልግሎት አሰጣጥ ጋር በየዘርፉ የሚታዩ ብልሹ አሰራሮች ለመፍታት የዕቅድ አካል አድርጎ ቀጣይነት ያለው ትግል ማድረግ እንደሚያስፈልግም በመድረኩ ላይ ተጠቁሟል ።

በውይይት መድረኩ ላይ የሆሳዕና ከተማ አስተዳደር ከንቲባ አቶ ዳዊት ጡምደዶ ፣የሀዲያ ዞን ከተማ ልማትና ኮንስትራክሽን መምሪያ ኃላፊ አቶ ተሾመ አናሞ ጨምሮ የከተማውና የቀበሌ አመራሮች ተሳትፈዋል ።

በነስሩ ባደዢ

Share this Post