05
Sep
2025
የውሃ ፋውንተን የተሠራበት ቦታ ከዚህ ቀደም ቆሻሻ የሚጣልበት ቦታ ስለነበር ሰዎች ለተለያዩ ተላላፊና ተላላፊ ባልሆኑ በሽታዎች ስጠቁ የነበረ ቦታ መሆኑን ጠቅሰው አሁን ግን መንግስት ቦታውን ለተለያዩ ለልማት አገልግሎት በማዋሉ ለብዙዎች የማዝናኛ ቦታ በመሆኑ ደስተኛ መሆናቸውን ገልጸዋል ።
በዕለቱም በስራ ቦታ ያገኘው ምህረቱ መለሰ ጠቅላላ ስራ ተቋራጭ ዋና ስራ አስካጅ አቶ ምህረቱ መለሰ በሰጡት አስተያየት ሴሌሜ የውሃ ፋውንቴን በውስጡ የተለያዩ ብሔር ብሔረሰቦችን ባህላዊ ሰናይ እሴቶችን በዉስጡ የያዘ መሆኑን ጠቅሰው የኮሪደር ልማት አጠቃላይ ስራዎችንም በተያዘለት ጊዜ ለማጠናቀቅ በትኩረት እየተሠራ እንደሆነም ተናግረዋል ።
በመጨረሻም የሆሳዕና ከተማ ምክትል ከቲባና የስራ ዕድል ፈጠራና ኢንተርፕራይዞች ልማት ጽ/ቤት ኃላፊ አቶ ታሪኩ ተከተልን ጨምሮ የዞንና የከተማ አመራሮችም ምልከታ አድርገዋል ።
በጌታቸው ደስታ