በማዕከላዊ ኢትዮጵያ ክልል የሆሳዕና ፖሊ ቴክኒክ ኮሌጅ ከሆሳዕና ከተማ አስተዳደር ሴቶችና ህፃናት ጉዳዮች ጽ/ቤት ጋር በመተባበር ለአቅመ ደካሞች ማዕድ ማጋራት እና ለተማሪዎች የትምህርት ቁሳቁስ ድጋፍ አድርጋዋል።

አክለውም የነገ አገር ተረካቢ የሆኑ ህፃናት በትምህርት ቁሳቁስ እጦት ምክንያት ሰፈር እንዳይውል ተቋሙ ለአንድ ዓመት የሚሆን የደብተርና እስክርቢቶ የትምህርት ቁሳቁስ ከ120 በላይ ለሚሆኑ ተማሪዎችና ከ60 በላይ ለሚሆኑ አቅመ ደካሞች ማዕድ የመጋራት ፕሮግራም አካሂደዋል ።

የሆሳዕና ከተማ አስተዳደር ሴቶችና ህፃናት ጉዳዮች ጽ/ቤት ኃላፊ ወይዘሮ በረከት ታደሳ በበኩላቸው በጎነት በሰውና በፈጣሪም ዘንድ ትልቅ ቦታ የሚሰጥ በጎ ተግባር መሆኑን ተናግረዋ ።

ዛሬ በሆሳዕና ፖሊ ቴክኒክ ኮሌጅ በኩል የተደረገው ማዕድ መጋራትና ለተማሪዎች የተደረገው የቁሳቁስ ድጋፍ በጣም ትልቅ ትርጉም ያለው ነው ብለው በትምህርት ቁሳቁስ እጦት ምክንያት የነገ ሀገር ተረካቢ የሆኑ ህፃናት ከትምህርት ገበታ ወደ ኋላ እንዳቀሩ ኮሌጁ ትልቅ ስራ መስራቱን ገልፀው መንግስታዊና መንግስታዊ ያልሆኑ የግል ድርጀቶችና ባለሀብቶችም በእንዲህ አይነት በጎ ተግባር ላይ እንድሳፉ ጥሪ አቅርበዋል ።

በማዕድ መጋራት ወቅት አስተያየት ከሰጡት መካከል ወ/ሮ ሳራ ላጵሶ ከቦቢቾ ቀበሌ እነ ወይዘሮ ደሳለች ይፍሩ ከሄጦ ቀበሌ በተደረገላቸው ድጋፍ ደስተኛ መሆናቸውን ገልፀው ምስጋናቸውን አቅርበዋል ።

በተመሳሳይ መልኩ ተማሪ ሳሙኤል አበራ ከሀቅሙራ ትምህርት ቤት እና ተማሪ ዳንኤል ጥጋብ ከሊች ጎጎ ትምህርት ቤት በተደረገላቸው ድጋፍ ደስታቸውን ገልፀዋል ።

በመጨረሻም በማዕድ መጋራት መርሐ ግብር ፕሮግራም ላይ የኮሌጁን ዲን ጨምሮ አስተዳደር ሰራተኞችና ባለ ድርሻ አካላት ተሳትፈዋል ።

በጌታቸው ደስታ

 

Share this Post