የከተማው ሰማጉ ጽ/ቤት የኑሮ ደረጃቸው ዝቅተኛ ሆኖ ዓመት በዓሉን ለመዋል እየተቸገሩ ላሉ ከ6ቱም ቀበሌዎች ለተመለመሉ 240 አቅመ ደካማ ወገኖች እና 150 ተማሪዎች ከ750 ሺህ በላይ በሆነ ወጪ የተዘጋጀላቸውን የተለያዩ የበዓል መዋያ ቁሳቁሶች ድጋፍ ማድረጉን ገለጿል ።
የከተማ አስተዳደሩ የሠራተኞችና ማህበራዊ ጉዳይ ጽ/ቤት ኃላፊው አቶ ተካልኝ አቦ ፕሮግራሙን በንግግር ሲከፍቱ ለችግረኞች እና ለአቅመ ደካማ የህብረተሰቡ ክፍሎች የተቻላቸውን ሁሉ በመደገፍ አለሁልህ ማለት ባህላችን ነው ።
አክለውም ኃላፊው ለ240 አቅመ ደካሞች ለእያንዳንዳቸው ምግብና ምግብ ነክ ነገሮች ለአብነትም 10 ኪሎ የዳቦ ዱቄት፣ 1ሊትር ዘይት፣ አንድ አንድ ኪሎ ፓስታ፣ መኮሪኒ፣ ሩዝ፣ ምስርና ጨው እንዲሁም የተለያዩ አልባሳት ሙሉ ፓኬጅ ተለግሶላቸዋል።
ከዚህም በተጨማሪ የመማር ፍላጎትና አቅም እያላቸው ለመማር ሁኔታዎች ላልተመቻቸላቸው ለ150 ህፃናትም የመማሪያ ቁሳቁሶችን በማደል የመማር ዕድላቸው እንዳይስተጓጎል ተደርጓል ።
በመጨራሻም ለዚህ መልካምና ለተቀደሰ አገልግሎት ተሳተፎ ያደረጉትን የቴዲ ዱቄት ፋብሪካን፣ ሊቻህብረት ሥራ ማህበርን ፣ በረከት ሆቴልን ፣ ገ/ፃዲቅ ሆቴልን ፣ ጡማ ፕላስቲክ ፋብሪካንና ሌሎችንም የህብረተሰብ ክፍሎች ከልብ አመስግነዋል ።
በዕለቱም ፕሮግራም ላይ የሀድያ ዞን የብልጽግና ፓርቲ ቅ/ጽ/ቤት ኃላፊና የመንግስት ዋና ተጠሪ አቶ ሳሙኤል ሽጉጤን ጨምሮ የዙኑ የብልጽግና ፓርቲ ቅ/ጽ/ቤት የርዕዮተ ዓለም ዘርፍ ኃላፊው አቶ መሳይ ተስፋዬ፣ የሆ/ከ/አስ/ር ከንቲባ አቶ ደዊት ጡምደዶ፣ የዞኑ የሰማጉ መምሪያና የከተማው ሰማጉ ጽ/ቤት ኃላፊዎችና ባለሙያዎች፣ የከተማና የቀበሌ አመራሮችና ሌሎችም ባለድርሻ አካላት ተሳትፈዋል ።
አንዳንድ ያነጋገርናቸው ድጋፍ የተደረገላቸውን አቅመ ደካሞችና የመማሪያ ቁሳቁሶች የተሰጣቸው ሕፃናት ተማሪዎች በየበኩላቸው በተቸገርንበት ወቅት ደርሳችሁልናል በማለት አክብሮታቸውን ገልጸዋል ።
የሆ/ከ/አስ/ር መ/ኮ/ጉ/ጽ/ቤት
ጳጉሜ 05/2017ዓ/ም
= በወንድሙ ደፋር =