12
Sep
2025
የሆሳዕና ከተማ አስተዳደር ከንቲባ አቶ ዳዊት ጡምዳዶ በበኩላቸው በሆሳዕና ከተማ የተሰራው የኮሪደር ልማት 98 ፐርሰንት መድረሱን አስታውሰው ከፊት ለፊት ባሉት ሳምታት የሳይክል መንገድ መስመር ስራ በማጠናቀቅ ለአገልግሎት ክፍት ለማድረግ እንደሚሰራ ነው የገለፁት።
ለሳይክል መስመር ስራ ግብዓት የሚሆነው ምርት ሀገር ውስጥ የማይገኝ በመሆኑ ስራው ሳይጠናቀቅ መቆየቱን ያወሱት ከንቲባው ከአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ጋር በመናበብና ልምድ በመውሰድ ምርቱ ሊገባ መቻሉን ተናግረዋል።
አጠቃላይ የኮሪደር ልማት ግንባታ ስራው እርስ በእርስ የተናበበ መሆኑን የገለፁት አቶ ዳዊት ለልማት ስራው መሳካት የከተማ አስተዳደሩ ከክልል፣ ከዞንና ከቀበሌ መዋቅሮች እንዲሁም ከህብረተሰቡ ጋር በመተባበር ስራውን ለፍፃሜ ለማድረስ ጥረት እየተደረገ መሆኑን አብራርተዋል።
የኮሪደር ልማት ስራውን ወደ መጨረሻ ምዕራፍ የደረሰ መሆኑና ቀሪ የሆነውን የሳይክል መስመር በአጭር ጊዜ ውስጥ አጠናቀው እንደሚያስረክቡ የተናገሩት ስራው የተረከቡት ተቋራጮች ናቸው።
የኮሪደር ልማት አካል የሆነው የሳይክል መስመር የሚሸፍነው 12 ነጥብ 4ኪ.ሜ መሆኑን ተመላክቷል።