የሆሳዕና ከተማ የውስጥ ለውስጥ አስፋልት መንገዶች ማስፋፊያ ፕሮጀክት አካል የሆኑ የነባር አስፋልት መንገድ የደረጃ ማሻሻያ 10ኪ.ሜ ፣ የሎት_2 እና ፌዝ_2 20 ኪ.ሜ መንገድና የሴች ዱና ቀበሌ ጤና ጣቢያ ግንባታ ፕሮጀክት ዲዛይን ላይ ገለጻና ውይይት መድረክ ተካሄደዋል ።

የሆሳዕና ከተማ የውስጥ ለውስጥ አስፋልት መንገዶች ማስፋፊያ ፕሮጀክት አካል የሆኑ የነባር አስፋልት መንገድ የደረጃ ማሻሻያ 10ኪ.ሜ ፣ የሎት_2 እና ፌዝ_2 20 ኪ.ሜ መንገድና የሴች ዱና ቀበሌ ጤና ጣቢያ ግንባታ ፕሮጀክት ዲዛይን ላይ ገለጻና ውይይት መድረክ ተካሄደዋል ።

የሆሳዕና ከተማ አስተዳደር መንግስት ኮሙኒኬሽን ጉዳዮች ጽ/ቤት ነሐሴ 13/2014 ዓ.ም

በውይይቱ ላይ የፌዴራል ፣ የክልል ተወካዮች ም/ቤት አባላት ፣ የዞን ፣የከተማው ፣ የቀበሌ አመራሮች ፣ የከተማው የአስፋልት መንገዶች ፕሮጀክት አማካሪ ምክር ቤት አባላትና የፕሮጀክት ጽ/ቤት ሠራተኞችና ሌሎችም ባለድርሻ አካላት ተሳታፊ ሆነዋል ።

የዕለቱን የውይይት መድረክ በንግግር የከፈቱ የሀዲያ ዞን ዋና አስተዳዳሪ አቶ አብረሃም መጫና የሆሳዕና ከተማ አስተዳደር ምክትል ከንቲባ አቶ በየነ ሸንቆ በየበኩላቸው የነባር አስፋልት መንገድ የደረጃ ማሻሻያ 10 ኪ.ሜ እና የ20 ኪ.ሜ አድስ መንገድ ግንባታ ፕሮጀክት ዲዛይን በአጠቃላይ እስከ 55 ኪ.ሜ የመንገድ አስፋልት ግንባታ ለመስራት ተቅደው እየተሠራ መሆኑንና ሌሎችም መጠነ ሰፊ መሠረተ ልማቶች ተጠናከሮ መቀጠል እንዳለበት አሳስበዋል ።

የከተማው ፕሮጀክት ጽ/ቤት ሥራ አስኪያጅ አቶ ደመቀ ኃይል በበኩላቸው በ2014 ዓ.ም በሚሠራው 14.134 ኪ.ሜ የውስጥ ለውስጥ ኮንክሪት የአስፋልት መንገድ እና ከአድስ ነባር መንገድ 5 ኪ.ሜ ጨምሮ 19.134 ኪ.ሜ የውስጥ ለውስጥ ኮንክሪት የአስፋልት መንገድ ለ2015 ዓመት ማለቅያና 2016 ዓ.ም መግቢያ አገለግሎት መስጠት እንደሚጀምር ተናግረዋል ።

ተሳታፊዎች የተሰጡ አስተያየት በከተማው መጠነ ሰፊ መሠረተ ልማቶች እየተሠሩ መሆኑን በማድነቅ እየተሠራ ያለው መንገድና ድርኔጆች በጥረት ላይ ትኩረት ተሰጥቶት የግንባታ ሥራ መሰራት እንደሚገባና በደቡብ መንገዶች ማስፋፊያ ቁጥጥርና ክትትል በቀረበው የመንገድና የጤና ግንባታ ዲዛይን ላይ ሀሳቦችን በመሸርሸር የበኩላችንን ድርሻ ልንወጣ ይገባል ስሉ ሀሳባቸውን ገልፀዋል ።

Share this Post