02
Nov
2022
የሆሳዕና ከተማ አስተዳደር ከንቲባ አቶ ሊሬ ጀማል እን ኤስኦኤስ ህፃናት መንደር ሀዋሳ ሆሳዕና አራዳ የመንግስት ያልሆነ የግል ድርጅት አቅመ ደካሞችንና ወላጅ አጥ ህፃናትን በኢኮኖሚና በማህበራዊ እንድሁም በምግብ ራሳቸውን እንድችሉ ላበረከቱት ድጋፍ በማመስገን የቤተሰብና የልማት ፕሮጀክት በመቻቸላቸው መሠረት በመቆጠብ ከተረጂነት ተላቀው ረሳቸውን በመቻል ለሌሎች መረዳት የሚችሉበትን አቅም በመጎልበት ተጠናክሮ መሥራት እንደሚገባ አሳስበዋል ።
ኤስኦኤስ ህፃናት መንደሮች ኢትዮጵያ የሀዋሳ ፕሮግራም ቢሮ የዳይሬክተር አቶ ፀጋዬ ደጃኔ በበኩላቸው ፕሮጄክቱ ከ42 ሚልዮን ብር በላይ በጀት ተበጅቶለት መጠነ ሰፊ ሥራዎችን በመስራት ላይ የሚገኝ ትልቅ ፕሮጀክት መሆኑን ጠቁመዋል ።
አክለውም የቤተሰብ እና የልማት ድርጅቱ
በህፃናት ላይ ትኩረት በማድረግ የወላጅን እንክብካቤ ለጡትና የወላጅን እንክብካቤ እንዳያጡ የመከላከል ሥራን በህብረተሰቡ ላይ በማጽረጽ የተለያዩ ድጋፎችን ሲያደርግ
የቆየው ፕሮጀክት መሆኑን ጠቅሰዋል ።
አንዳንድ አስተያየት የሰጡት ኤስኦኤስ ህፃናት መንደር ሐዋሳ ሆሳዕና አራዳ ፕሮጀክት ልጆቻቸውን የማማሪን ዕድል ያገኙበትና ለሁለት ትምህርት ቤቶች እንድሁም ለተለያዩ ተቋማት የተለያዩ የቢሮና የትምህርት ቁሳቁስ ላበረከቱት ድጋፍ አመስግነዋል ።