21
Sep
2022
የከተማ አስተዳደር መንግስት ኮሙኒኬሽን /ጉዳዮች /ጽ/ቤት መስከረም 10/2015 ዓ.ም
በቀበሌው ተስፋ አለን የልማት ቡድን ያሆዴ የሀዲያ ብሔር የዘመን መለወጫ በዓል ምክንያት በማድረግ ከጎንዮሽ ቁጠባ 126,231 ብር እና 30 ኪሎ ግራም ቡና ለአባላቱ አከፋፍሏል ።
የከተማው ሴቶችና ህፃናት ጉዳይ ጽ/ቤት ኃላፊ ወ/ሮ በረከት ታደሰ በፕሮግራሙ ላይ እንደገለጹት በቀበሌው በቡድን የተደራጁ ሴቶች ቁጠባን ባህል በማድረግ የልማት ቡዱኑ ኢኮኖሚና ማህበራዊ ተፅእኖ ፈጠራ በመሆን ወደ ህብረት ሥራ ማህበር መሸጋገር እንደለበት በመጠቆም መልካም ተሞክሮ ለማስፋት ጥረት ማድረግ እንዳለበትም አሳስበዋል ።
የሴች ዱና ቀበሌ አስተዳደር ሴቶችና ህፃናት ጉዳይ ጽ/ቤት ኃላፊ ወ/ሮ ገነት ቅጣው በበኩላቸው በቀበሌው 2014 ዓ.ም ውጤታማ ከሆኑ የሴቶች ልማት በድኖች መካከል የተስፋ አለን የሴቶች የልማት ቡድኖች እንደሚገኙበት ገልፅዋል ።
አክለውም ቡድኖቹ ከጎንዮሽ ቁጠባ በተጨማሪ ወደ ህብረት ሥራ ማህበር ለመሸጋገር ተጠናከሮ እየሠሩ መሆኑንና መደበኛ ቁጠባ ከ85 ሺ ብር በላይ መቆጠብ መቻላቸውን ተናግረዋል ።
በፕሮግራሙ ላይ በከፍተኛ ደረጃ በመቆጠብ ግንባር ቀደም ለሆኑ አባላት ዕውቅና ስጦታ ተሰጥቷል ።