የሆሳዕና ከተማ አስተዳደር የወጣቶች ማህበር ከ150 በላይ አቅመ ደካሞች የማዕድ መጋራት ድጋፍ አደረገ ።

የሆሳዕና ከተማ አስተዳደር የወጣቶች ማህበር ከ150 በላይ አቅመ ደካሞች የማዕድ መጋራት ድጋፍ አደረገ ።

የሆሳዕና ከተማ አስተዳደር መንግስት ኮሙኒኬሽን ጉዳዮች ጽ/ቤት ነሐሴ 23/2014 ዓ/ም

የሆሳዕና ከተማ አስተዳደር ወጣቶችና ስፖርት ጽ/ቤት ኃላፊ አቶ ፍሰሀ ታደሰ እንደገለፁት የወጣቶች ማህበር በራስ ተነሳሽነት ላደረጉት በጎ ተግባር በማመስገን በእንደዚህ በጎ ተግባርን ለመስቀጠል ሌሎችም አካላት ማዕድ ማጋራት የኢትዮጵያን መልካምነታችን ነው ሲሉ ጠቅሶ በቀጣይነት በአዘቦት ቀናትም እንዲሆን ተደጋግፎ መሥራት እንዳለባቸው አሳስበዋል ።

የማህበር ስብሰብ ወ/ት ስንታየሁ አለማየሁ በበኩላቸው ማህበሩ ከዚህ በፊትም በየጊዜው ምግብና ውሃ ከባለሀብቶች በመሰብሰብ መጠነ ሰፊ ተረጂዎችን ድጋፍ እያደረገ ያለው መሆኑን ጠቁመው ከ150 በላይ አቅመ ደካሞችን የምግብ መጋራትና በቀጣይነት በላው መልኩ ከጎናችሁ ነን ስሉ ተናግረዋል ።

Share this Post