22
Sep
2022
የሆሳዕና ከተማ አስተዳደር መንግስት ኮሙኒኬሽን ጉዳዮች ጽ/ቤት መስከረም
11/2015 ዓ.ም
የቦብቾ ቀበሌ የአስተዳደር ተወካይ አቶ ተመስገን ወርቁና የቀበሌው ሴቶችና ህፃናት ጽ/ ኃላፊ ወ/ሮ ክብነሽ ሶድሶ በየበኩላቸው አቅመ ደካማ አረጋዊያንና የዘማች ቤተሰብ መካከል ለተወጣጡ ተረጂዎች ያሆዴ የሀዲያ ብሔር ዘመን መላወጫ በዓልን ምክንያት በማድረግ በገንዘብና ቀዓይነት ድጋፍ ማድረጋቸውን ገልፀዋል ።
አክለውም ኃላፊዎቹ ለተረጂዎቹ የምግብ ዱቄት ፣ የትምህርት ቁሳቁስ ደብተር ና እስክርቢቶ በብር ግምት ከ70 ሽህ ብር ባለይ ግምት ያላቸው ቁሳቁሶችና 30,000 ብር ስሆን በድምሩ ከ100,000 ሽ ብር በላይ ድጋፍ ማድረጋቸውን ተናግረዋል ።
የሆሳዕና ከተማ አስተዳደር ሴቶችና ህፃናት ጽ/ቤት ኃላፊ ወ/ሮ በርከት ታደሰ እንደገለፁት ለተረጂዎቹ ለተደረገው ድጋፍ ምስጋና በማቅረብ ዝቅተኛ ገቢያላቸው የህብረተሰብ ክፍሎች በተለያዩ ስራዎች በመሳተፍ በዘላቂነት ራሳቸውን ለማቋቋም መስራት እንደሚገባ አሳስበዋል ።
በተለይም የዋቸሞ መካከለኛ ክሊኒክ ባለቤት ደምሳሽ ተመስገን ለ10 አራጋዊያን በዓሉን እንዲያከብሩ ለእያንዳንዱ አንድ አንድ ሽ ብር እና በየወሩ 300 መቶ ብር ቋም ደመወዝ እንዲያገኙ ለባረከታላቻው ተረጂዎቹ ምስጋና አቅርበዋል ።