በሆሳዕና ከተማ የሊች አምባ ቀበሌ አስተዳዳር የአድስ ዓመት በዓልን ምክንያት በማድረግ ከ150 ሺህ ብር በላይ ወጪ በማድረግ ለአረጋዊያንና አቅመ ደካሞች ማዕድ ማጋራት ፕሮግረም አድርጋዋል።

ዛሬ የተደረገው ማዕድ መጋራትና የቁሳቁስ ድጋፍ ታላቁ የኢትዮጵያ ህዳሴ ግድብ ግንባታ ተጠናቆ በተማረቀበት ማግስት መሆኑን ጠቅሰው ከዚህ በኋላ በሁሉም ዘርፍ ጠንክረን ከሰራን ኢትዮጵያ ረጂ እንጂ ተረጂ አትሆንም በማለት መልካም ምኞታቸውን ገልጸዋል ።

የሊች አምባ ቀበሌ ዋና አስተዳዳር አቶ ደሳለኝ ሞሎሮ በበኩላቸው "በጎነት ለኢትዮጵያ ከፍታ"በሚል መሪ ቃል በጠቅላይ ሚኒስተር አብይ አህመድ (ዶ/ር) መሪነት በሀገር ደረጃ የተጀመረው በጎ ተግባር አንዱ ለአንዱ ያለውን በማካፈል ማረዳዳትንና አብሮ መብላትን መንፈስ የፈጠራ ተግባር መሆኑን አንስተዋል ።

በጎነት ውስጥ መረዳዳት፣መተጋገዝ ፣አብሮትና አንድነት አሌ ያሉት አቶ ደሳለኝ አድሱን ዓመት ስንቀበል ከአቅመ ደካሞችና አረጋዊያን ጋር ያለንን ተካፍለን በማብላትና በመረዳዳት መሆን እንዳለበት አሳስበዋል

የሊች አምባ ቀበሌ ሴቶችና ህፃናት ጉዳዮች ጽ/ቤት ኃላፊ ወ/ሮ መኪያ ጀማል በዕለቱ ማዕድ ማጋራትን አስመልክተው በሰጡት አስተያየት በጎነት ለራስ ነው ብለው ዛሬ የተደረገው ድጋፍ የቀበሌን ባለሀብቶችና ነዋሪዎችን በማስተባበር በተገኘው ገንዘብ የተደረገ ድጋፍ መሆኑን አንስተዋል ።

ወይዘሮ መኪያ አክለውም ከ40 በላይ ለሆኑ አረጋዊያንና አቅመ ደካሞች ከተደረገው ድጋፍ በተጨማሪ በቤታቸው ድጋፍ የተደረገላቸው መኖሩን ገልፀው በዕለቱም ለበዓል የሚሆን ዶሮ፣ሽንኩርት፣ዱቄትና ሌሎች አልባሳትም ድጋፍ መደረጉን ገልጸዋል ።

በማዕድ መጋራት ወቅት አስተያየት ከሰጡት መካከል ወይዘሮ አማረች አኑሎ እነ ወይዘሮ መለሰች መኮሮ በተደረገላቸው ድጋፍ ደስተኛ መሆናቸውን ገልፀው ምስጋናቸውንም አቅርበዋል።

በመጨረሻም በማዕድ መጋራት መርሐ ግብር ፕሮግራም ላይ የከተማ አስተዳዳር ሴቶችና ህፃናት ጉዳዮች ጽ/ቤት ኃላፊን ጨምሮ የከተማና የቀበሌው ባለ ድርሻ አካላት ተሳትፈዋል ።

በጌታቸው ደስታ

የሆሳዕና ከተማ አስተዳደር መንግስት ኮሙኒኬሽን ጉዳዮች ጽ/ቤት ጳጉሜ 05/2017 ዓ.ም

Share this Post