09
Sep
2022
የሆሳዕና ከተማ ወጣቶችና ስፖርት ጽ/ቤት ከኢትዮጵያ ካቶሊካዊት ቤተክርስቲያን ማህበራዊና ልማት ኮሚሽን ጋር በመተባበር ለ200 አቅመ ደካማ አረጋውያን የምግብ እህል ድጋፍ አደረገ።
የሆሳዕና ከተማ አስተዳደር መንግስት ኮሙኒኬሽን ጉዳዮች ጽ/ቤት ጳጉሜ 4/2014 ዓ.ም
የከተማ ወጣቶችና ስፖርት ጽ/ቤት ኃላፊ አቶ ፍሰሐ ታደሰ እንደገለፁት በከተማው ከሚገኙ ስድስት የቀበሌ አስተዳደሮች ለተወጣጡ ተረጂዎች ለእያንዳንዳቸው የዘመን መለወጫ በዓል ምክንያት በማድረግ 25 ኪሎ ግራም በቆሎ ድጋፍ ተደርጓል ።
የሆሳዕና ከተማ ብልጽግና ፓርቲ ጽ/ቤት የመንግስት ረዳት ተጠሪ አቶ ዳዊት መሀመድ በበኩላቸው ለተረጂዎቹ ለተደረገው ድጋፍ ምስጋና በማቅረብ ዝቅተኛ ገቢ ያላቸው የህብረተሰብ ክፍሎች በከተማ ሴፍትኔትና በተለያዩ ስራዎች በመሳተፍ በዘላቂነት ራሳቸውን ለማቋቋም መስራት እንዳለባቸው አሳስበዋል ።
አንዳንድ ተረጂዎች በሰጡት አስተያየት በዚህ አስቸጋሪ ወቅት ለተደረገላቸው ድጋፍ ምስጋና አቅርበዋል ።