06
Oct
2022
የከተማው የመንግስት ኮሙኒኬሽን ጽ/ቤት መስከረም 25/2015 ዓ.ም
በመድረኩ ለይ የ2014ዓ.ም የክረምት ወራት የወጣቶች የበጎ ፈቃድ አገልግሎት የአፈጻጸም ሪፖርት ቀርቦ ውይይት ተደርጎበታል ።
የከተማው ወጣቶችና ስፖርት ጽ/ቤት ኃላፊ አቶ ፍሰሐ ታደሰ እንደገለጹት ለሁለት ተከታታይ ወራት በተካሄደው የክረምት የወጣቶች የበጎ ፈቃድ አገልግሎት በ14 የአገልግሎት ዘርፎች የተለዩ የልማት ሥራዎች ተከናውነዋል ።
አክለውም ከልማት ስራዎቹ መካከል የከተማ ፅዳትና ውበት፣ የክረምት ወራት ማጠናከሪያ ትምህርት ፣የችግኝ ተከላ፣ የደም በልገሳ ፣የመንገድ ደህነት፣የስፖርት እና ሌሎችም እንደሚገኙበት ገልፀዋል ።
የከተማው የመንግስት ዋና ተጠሪ አቶ ሳሙኤል ታደሰ በበኩላቸው ወጣቶች ከበጎ ፈቃድ አገልግሎት ባሻገር የሀገራችን ሉአላዊነት ለማስከበር ወደርየለሽ ሚና በመጫወት ላይ መሆናቸውን ጠቅሰው በጎነት ለራስ በመሆኑ የጀመሩት አርዓያነት ያለው ተግባር አጠናክረው እንዲቀጥሉ አሳስበዋል ።