20
Oct
2022
ጥቅምት 10/2015 ዓ.ም
የጽ/ቤቱ ኃላፊ ወ/ሮ በረከት ታደሰ እንደገለጹት ጽ/ቤቱ በዞን ደረጃ ከአቻ ሴክተሮች ተወዳድሮ ግንባር ቀደም እንዲሆን አስተዋጽኦ ላበረከቱ የጽ/ቤቱ ባለሙያዎችና ባለድርሻ አካላት ምስጋና አቅርበዋል ። በበጀት ዓመቱ ጽ/ቤቱ በሴቶች የልማት ቡድን በክልል ደረጃ ሁለተኛ በመውጣት የዋንጫ ተሸላሚ መሆኑንም ጠቁመዋል ።
የሆሳዕና ከተማ አስተዳደር የመንግስት ዋና ተጠሪ ዶ/ር ደበበ ገብሬ በበኩላቸው ጽ/ቤቱ ተግባርን በተግባር በማረጋገጥ የዋንጫ ተሸላሚ በመሆኑ ሳይዘናጋ የሴቶችና ህፃናት ኢኮኖሚያዊ ተጠቃሚነት ለማረጋገጥ ተጠናክሮ እንዲቀጥልም አሳስበዋል ።
አክለውም የጽ/ቤቱ ውጤታማ ተሞክሮ በመቀመር በሁሉም ሴክተሮች ውጤታማ የተግባር አፈፃፀም እንዲኖር እንደሚሠራም ጠቁመዋል ።