የደቡብ ብሔር ብሔረሰቦች ህዝቦች ክልል ምክር ቤት ቋም ኮሚቴ ከሆሳዕና ከተማ ምክር ቤት ጋር የከተማ ምክር ቤት አደረጃጀት መዋቅር ያለበት ደረጃ የመፈተሽና ወቅታዊ የትምህርት ፣ የጤና ፣ ግብርና ሥራዎችንና አጠቃላይ በ2014 ዓ.ም ተግባራት አፈጻጸም ዙርያ ውይይት መድረክ ተካሄደዋል ።

የሆሳዕና ከተማ አስተዳደር መንግስት ኮሙኒኬሽን ጉዳዮች ጽ/ቤት ጥቅምት 18/2015 ዓ.ም

የሆሳዕና ከተማ ምክር ቤት ዋና አፈ -ጉባኤ ሙሉነሽ ሴድሶ እንደገለፁት በየደረጃው የሚገኙ ጠንካራ ጎኖችንና ክፍተቶችን በመለየት በጥንካሬ የተለዩ ተግባራትን ቀጣይነት መረጋገጥ የሚያስችል ሥራ እየተሠራ ያለው መሆኑን ጠቁመው የተለዩ ውስንነቶችን ለመቅረፍ በየደረጃው ከሚገኙ ባለድርሻ አካላት ጋር ቅንጅት በመፍጠር የማረምና የማስተካከል ሥራዎች ተሠርቶል ስሉ ገልጸዋል ።

አክለውም ዋና አፈ-ጉባኤ የትምህርት ወቅታዊ ተግባራት ላይም ከአድሱ ፍኖተ ካርታ ጋር ተያይዞ በዘላቂነት የሚሠራ ስራ እንደመሆኑ መጠን ለመሥራትም በቋም ኮሚቴ በኩል የሚደረግ የክትትልና ቁጥጥር ሥራ ለማከናወን የሚያስችል ምቹ ሁኔታን በመፍጠር የዝግጅት ምዕራፍ መጠናቀቁን ጠቁመዋል ።

በመጨረሻም በየደረጃው የሚገኙ ምክር ቤቶች ጠንካራና ተሰሚነት ያላቸው የህዝብ ውክልና ሥራ በአግባቡ በመሥራት ችግር ፈቺ አቅም ያላቸው ቋም ኮሚቴ አባለት እንደሆነና ለቀጣይ መጠነ ሰፍ ሥራዎችን በመሥራት ላይ መሆናቸውን ተናግረዋል ።

Share this Post