02
Nov
2022
የጽ/ቤቱ ኃላፊ ወ/ሮ ፀጋነሽ ዮሐንስ እንደገለጹት በከተማው በተጠናቀቀው የበጀት ዓመት 534 ሚሊየን 573ሺ 280ብር መሰብሰብ መቻሉን ጠቁመው ገቢው ካለፈው ዓመት ተመሳሳይ ወቅት ሲነፃፀር የ145ሚሊየን 530ሺ 633ብር ብልጫ የለው ውጤታማ ሥራ መከናወኑን ተናግረዋል ።
አመራሩና ባለሙያው ተቀናጅቶ በዘርፉ የሚታዩትን የኪራይ ሰብሳቢነት ችግሮች በመፍታት በ2015 የበጀት ዓመት የታቀደው ከ750 ሚሊየን ብር በላይ ለመሰብሰብ ትኩረት ተሰጥቶ እየተሰራ መሆኑንም ኃላፊዋ ጨምረው ገልፀዋል ።
የሆሳዕና ከተማ አስተዳደር የመንግስት ዋና ተጠሪ ዶ/ር ደበበ ገብሬ በበኩላቸው በገቢ አሰባሰብ ዘርፍ ከፍተኛ ውጤት እንዲመዘገብ አስተዋጽኦ ላበረከቱ የጽ/ቤቱ ሠራተኞችና ባለድርሻ አካላት በማመስገን ከከተማው የልማት ፍላጎት አንፃር የገቢ አሰባሰቡን በውጤት ታጅቦ ቀጣይነት ሊኖረው እንደሚገባም አሳስበዋል ።
በመጨረሻም በጉባኤው ላይ በገቢ አሰባሰብ ዙሪያ ውጤት እንዲመዘገብ አስተዋጽኦ ላበረከቱ ተቋማትና ግለሰቦች ሽልማትና ዕውቅና ተሰጥቷል ።