የሆሳዕና ከተማ መንግስት ኮሙኒኬሽን ጉዳዮች ጽ/ቤት ጥቅምት 30/2015 ዓ.ም
የሆሳዕና ከተማ አስተዳደር የመንግስት ረዳት ተጠሪ አቶ አድሴ ኢፋ እንደገለፁት የከተማው ሴቶችና ህጻናት ጉዳይ ጽ/ቤት በ2014 ላይ ዘርፍ ብዙ ተግባራት ላይ ውጤታማ በመሆን በሀዲያ ዞን ከሚገኙ ወረዳዎችና ከከተማ አስተዳደሮች ግንባር ቀደም ነው ስሉ ጠቅሰው በ2015 በጀት ዓመትም ላይ ግንባር ቀደምነትን ለማስቀጠል ሁሉም ባለድርሻ አካላት በቅንጅት መሥራት እንደሚገባ አሳስበዋል ።
የሆሳዕና ከተማ አስተዳደር ሴቶችና ህፃናት ጉዳይ ጽ/ቤት ኃላፊ ወ/ሮ በርከት ታደሰ በበኩላቸው የሴቶችና የህፃናት መብትና ጥቅሞችን በማስከበር በኢኮኖሚ ማሀበራዊና ፖለቲካዊ ተሳትፎና ተጠቃሚነት ለማጎልበት በኢኮኖሚና ማህበራዊ እንቅሰቃሴዎች ዉስጥ በንቃት ለማሳተፍ የሚያስችሉ እድሎች የተመቻቸ መሆኑን ጠቁመዋል ።
አክለውም በሴቶችና ህፃናት ላይ የሚፈፀሙ ጥቃቶችን መከላከል እንዲቻል ለማህበረሰብ ግንዛቤ መፍጠር ቅድሚያ የሚሰጥ ተግባር ነው ስሉ ጠቅሰው በ2014 ዕቅድ አፈጻጸም ላይ በውስንነት በተገመገሙበት ተግባራትን በ2015 በጀት ዓመት ዕቅድ ጋር ትኩረት ተሰጥተው ለመሥራት ታቅደው እየተሠራ ነው ስሉ ተናግረዋል ።
ከአንዳንድ ተሳታፊዎች የተጠ አሰተያየት የሴቶችና ህፃናት ጉዳይ ጽ/ቤት ላይ ዘርፍ ብዙ ተግባራት ባለው ልክ በበጀት መደገፍ እንዳለበትና የሴቶችን ልማት ቡዱን ወደ ህብረት ሥራ ለማሸጋገር ተጠናከሮ መሥራት ይገባል ብላዋል ።
በመጨረሻም በ2014 በጀት ዓመት በአጠቃላይ ሥራ አፈጻጸም ላይ ከስድስቱም ቀበሌያት መካከል 1ኛ አራዳ ቀበሌ 2ኛ ቦብቾ ቀበሌ 3ኛ ሄጦ ቀበሌ እንዲሁም በከተማው ከሚገኙ የግል ድርጀቶች ግንባር ቀደም የSOS የሆሳዕና አራዳ የህፃናት ፕሮጀክት ጽ/ቤት ሲሆን ከከተማው ጽ/ቤት ባለሙያዎች መካከል 1ኛ ለአበበ ሰዎሬ 2ኛ ወ/ሪት ቅድስት አርጋው 3ኛ ለአቶ ዳዊት አበበ ባለሙያዎች ግንባር ቀደመ ለሆኑት የዕውቅና ሰርተፍኬት ተሰጥተዋል ።