በ2014 ዓ.ም በተካሄደው የአረንጓዴ አሻራ መርሃ ግብር 82.5 ሚሊዮን ችግኞች መተከሉን የሀዲያ ዞን ግብርና መምሪያ አስታወቀ

በ2014 ዓ.ም በተካሄደው የአረንጓዴ አሻራ መርሃ ግብር 82.5 ሚሊዮን ችግኞች መተከሉን የሀዲያ ዞን ግብርና መምሪያ አስታወቀ

መስከረም 6/2015 ዓ.ም (የሀዲያ ዞን መ/ኮ/ጉ/መምሪያ)

በዞኑ አሻራችን ለትዉልዳችን በሚል መሪ ቃል በተካሄደው የችግኝ ተከላ መርሃግብ ከ1.7 ሚሊዮን በላይ የተለያዩ የህብረተሰብ ክፍሎች መሳተፋቸው ተጠቁሟል።

የሀዲያ ዞን ግብርና መምሪያ ም/ል ኃላፊና የተፈጥሮ ሀብት ልማት ዘርፍ ኃላፊዉ አቶ ታገሳ ተመስገን እንዳሉት÷ በኢፌዲሪ ጠቅላይ ሚኒስተር ዶ/ር አቢይ አህመድ ሀሳብ አመንጪነት የችግኝ ተከላው ላለፉት 4 ዓመታት በሀገር ደረጀ መካሄዱን ጠቁመዋል።

በሀዲያ ዞን 4ኛ ዙር የችግኝ ተከላ መርሃ ግብር መነሻ ላይ በሁሉም ደረጀ ላሉ የህብረተሰባችን ክፍል ግንዛቤ በመፍጠር ወደ ትግበራ መገባቱን ተናግረዋል።

በመርሃ ግብሩ የተለያዩ አደረጃጀቶች መንግስታዊና መንግስታዊ ያልሆኑ ተቋማት ፣ የወጣቶችና የሴት አደረጃጃቶች ፣ ተማሪዎችና አርሶ አደሮች መሳተፍ መቻላቸው ገልጸዋል።

በመሆኑም ማህበረሰቡ በባለቤትነት መንፈስ በተግባሩ የተሳተፋበት ሁኔታ አበረታች እንደነበር አንስተዋል።

በዚህም በ2014 ዓ.ም 90 ሚሊዮን ችግኝ ለመትከል ታቅዶ 82.5 ሚሊዮን ችግኝ መተከሉን አቶ ታገሰ ተመስገን ገልፀዋል።

በችግኝ ተከላው የተለያዩ የፍራፍሬ ተክሎች ፣ ለእንሰሳት መኖ የሚዉል ሣርና እንዲሁም ለጥላና በከተማ አካባቢዎች ለዉበት የሚጠቅሙ ዝንባባና ሌሎችም የችግኝ አይነቶች መተከላቸውን ተናግረዋል።

ችግኞቹ ለየትኛው የአየር ጠባይ ምን ዓይነት ችግኝ ሊስማማ እንደሚችል በጥናት ተለይቶ እንደየ አካባቢው የዓየር ጠባይ መተከሉን ገልፀዋል።

የተተከሉት ችግኞች ደህንነታቸዉ ተጠብቆ ፀድቀው ለታለማላቸዉ ዓላማ እንዲዉሉ የሚመለከታቸዉ አካላት ጥበቃ እንዲያደርጉ ጠይቀዋል።

በኤልያስ ተሰማ

Share this Post