09
Sep
2022
የሆሳዕና ከተማ አስተዳደር ም/ ከንቲባ አቶ በየነ ሸንቆ የ2015 ዓ.ም የዘመን መለወጫ በዓል ምክንያት በማድረግ የእንኳን አደረሳችሁ መልዕክት አስተላልፈዋል ።
የከተማው የመንግስት ኮሙኒኬሽን ጽ/ቤት ጰጉሜ 04/2014 ዓ.ም
አቶ በየነ ሸንቆ በመልዕክታቸው የከተማችን የተለያዩ የህብረተሰብ ክፍሎች በዓሉን ሲያከብሩ የዘማች ቤተሰቦች ፣ አቅመ ደካሞችና በጦርነቱ የተፈናቀሉ ወገኖቻችን በመርዳት መሆን እንዳለበትም ጠቅሰዋል ።
የከተማችን ነዋሪዎች የሀገራችን ሉአላዊነትን ለማስከበር የህይወት መስዋት ለሚከፍለው መከላከያ ሠራዊት ላደረገው ከፍተኛ ድጋፍ በማመስገን ድጋፋቸውን በሌሎች የልማት ሥራዎች አጠናክረው እንዲቀጥሉ አሳስበዋል ።
አክለውም ህብረተሰቡ የእርድ እንስሳት ተረፈ ምርቶች በተገቢው በማስወገድ የአካባቢውን ንፅህና ሊጠብቅ እንደሚገባም በመልዕክታቸው ጠቁመዋል ።