የሆሳዕና ከተማ አስተዳደር ትራንስፖርት ጽ/ቤት ለ2015ዓ.ም ያሆዴ የሀዲያ ብሔር የዘመን መለወጫ በዓል እንኳ በሠላምና በጤና አደረሳችሁ እያለ መልካም ምኞቱን ያስተላልፋል ።

የከተማው የመንግስት ኮሙኒኬሽን ጽ/ቤት መስከረም 09/2015 ዓ.ም

የጽ/ቤቱ ኃላፊ አቶ ግዛቸው ጋዶሬ ባስተላለፉት መልዕክት በሀገር ውስጥና በውጭ አገር ለምትገኙ የሀዲያ ብሔር ተወላጆች በሙሉ አዲሱ ዓመት የሠላም፣የጤና፣ የአብሮነት፣የአድነትና የብልፅግና ጊዜ እንዲሆንላችሁ ምኞታቸውን ገልፀዋል ።

በአዲሱ የበጀት ዓመት በከተማው የሚታየውን የመናኸሪያ ጥበት ለመፍታት ጥምር የትራንስፖርት ማህበራትና ህብረተሰቡን በማስተባበር ቀደም ሲል የሆሳዕና ማረሚያ ተቋም ሲገለገልበት በነበረው ቦታ ላይ የዘመናዊ መናኸሪያ ግንባታ ለማስጀመር የሚያስችሉ የገንዘብ ማሰባሰብና ሌሎች የቅድመ ዝግጅት ሥራዎች እየተከናወኑ መሆኑንም ተናግረዋል ።

በጽ/ቤቱ ከአገልግሎት አሰጣጥ ጋር በተያያዘም በዘርፉ የሚታዩ የመልካም አስተዳደር ችግሮች ለመፍታት ትኩረት ተሰጥቶት እየተሰራ መሆኑን የገለጹት ኃላፊው ህብረተሰቡ የትራንስፖርት አገልግሎት በሚጠቀምበት ወቅት በትርፍነት ባለመጫን ፣ከታሪፍ በላይ ባለመክፈል እንዲም መሰል ችግሮች ሲያጋጥሙት ለሚመለከተው የህግ አካል ጥቆማ በመስጠት የበኩሉን አስተዋጽኦ ማበርከት እንዳለበትም መልዕክት አስተላልፈዋል ።

በመጨረሻም በያዝነው ወር መጨረሻ የሚሰጠውን አገር አቀፍ የ12ኛ ክፍል ፈተና የሚወስዱ ተማሪዎችን ወደ ተለያዩ ዩኒቨርስቲ ዎች ለማድረስ ከሚመለከታቸው የትራንስፖርት ማህበራት ጋር በመነጋገር የተሽከርካሪዎች ዝግጅት በማደረግ ላይ መሆኑንም ኃላፊው ጠቁመዋል ።

Share this Post