22
Sep
2022
የሀዲያ ዞን ምክር ቤት ዋና አፈ ጉባኤ ወይዘሮ እቴነሽ ሙሉጌታ ለ2015 ዓ.ም የሀዲያ ብሔር ዘመን መለወጫ "ያሆዴ" በዓል የእንኳን አደረሳችሁ በማለት በዓሉ የሰላም የፍቅር የአብሮነትና የብልጽግና እንዲሆን መልካም ምኞታቸውን ገልጸዋል።
ዋና አፈ ጉባኤዋ በዓሉን አስመልክቶ በሰጡት መግለጫ የሀዲያ ህዝብ በያሆዴ በዓል በአዲስ የተስፋ ብርሃን የሚበላበት፣ ያለፈውን ዓመት ወደ ማይመለስበት አሰናብቶ ለአዲሱ ዓመት ራሱን የሚያዘጋጅበት በጉጉትና በናፍቆት የሚጠበቅ ነው ብለዋል።
"ያሆዴ" ከምንም በላይ ለሀዲያ ህዝብ የሁሉም ነገር መጀመሪያው እንደሆነም አንስተዋል።
የዞኑ ምክር ቤት ከዞኑ ህዝብ ይሁንታ አገኝቶ የተቋቋመ እንደመሆኑ መጠን በአዲሱ ዓመት አዲስ የሥራ መንፈስ በመላበስ የህዝቡን የመልማትና የመልካም አስተዳደር ችግሮችን ለመፍታት ከምን ጊዜውም በላይ የአስፈጻሚ አካላት ክትትልና ቁጥጥር አጠናክሮ ይቀጥላል ብለዋል።
በመጨረሻም በሀገር ውስጥና በውጭ ለሚኖሩ የብሔሩ ተወላጆች በሙሉ የእንኳን ለ2015 ዓ.ም ለሀዲያ የዘመን መለወጫ "ያሆዴ" በዓል በሠላም አደረሳችሁ በማለት መልካም ምኞታቸውን ገለፀዋል ።
አዲሱ ዓመት የሠላም ፣የፍቅር የጤና አንዲሁም የብልጽግና እንዲሆንም ተመኝተዋል ።