የመምሪያ ኃላፊዎች እንኳን ለ2015 ዓመት ለ"ያሆዴ" በዓል በሰላም አደረሳችሁ መልዕክት አስተላልፏል።

የሀድያ ዞን ትምህርት መምሪያ ኃለፊ ዶ/ር አበበ ሎለሞ በበኩላቸው ያሆዴ በማይዳሳሱ በዓለም ቅርስነት (በዩኔስኮ) እንዲመዘገብ የብሔሩ ተወላጅ በሙሉ ድርሻ እንዳለው በመጥቀስ

አዲሱ የትምህርት ሥርዓት በራሳቸው ባህልና አካባቢያዊ ሁኔታ ቃኝተው እንደተዘጋጀው መጠን በሁሉም ትምህርት ተቋማት ስለ ያሆዴ ምንነት ለዜጎች ግንዛቤ በመፍጠር የትምህርት ዘርፍ የበኩሉን ድርሻ እንዲወጣ መልዕክት አስተላልፏል።

የሃዲያ ዞን ሠላምና ፀጥታ መምሪያ ኃላፊ አቶ አረጋ ማዴቦ ባስተላለፉት መልዕክት የያሆዴ በዓል የማህበረሰቡን ማንነትን የሚያጎላ ከመሆኑ መጠን በዓሉ በማህበረሰቡ ዘንድ በጣም ተወዳጅነትና ተቀባይነት ያለው ስለሆነ መላው ማህበረሰቡ በዓሉን በሚያከብርበት ወቅት ምንም ዓይነት የፀጥታ ችግር እንዳይፈጠር የፀጥታ አካላት መላው ህብረተሰብ ጋር በጋራ በመሆን ቅድሚያ ስራዎች እየተሰራ ይገኛል ።

በዓሉ የሰላምና የመቻቻል እንድሆን ለመላው ማህበረሰብ ቀድሞ የግንዛቤ ማስጨበጫ ስራዎች በተቀናጀ መልኩ እየተሰራ መሆኑን ተነግሯል ።

በዓሉን ምክንያት በማድረግ ወደ አከባቢያችን የሚገባ ማንኛውም ዓይነት ፀጉር ልውውጦችን ህብረተሰብ አካባቢውን በንቃት በመጠበቅ በዓሉ የሰላም እንድንሆን የበኩላቸውን እንድወጡ አሳስበዋል ።

የሀዲያ ዞን ወጣቶችና ስፖርት መምሪያ ኃላፊ ተሻለ ደሳኝ ያሆዴ በዓልን ለማድመቅና ሕዝባዊ መሠረት ለማስያዝ ቱር ያሆዴ የተሰኘ የባህል ቡድን ከሰሞኑ በተለያዩ የወረዳና የከተማ አስተዳደሮች በማስተዋወቅ እና በመንቀሳቀስ መቆየቱ በማስታወስ ።

አሁንም የያሆዴን በዓል ለመላው ማህበረሰብ በማስተዋወቅና አከባቢውን በማጽዳት ሰፊ ስራ እየተሰራ ይገኛል ።

የያሆዴን በዓል የስፖርት አካል በማድረግ " ባህሌን እጠብቃለሁ ለያሆዴ ሮጣለሁ " በሚል መሪ ቃል ከዚህ ቀደሞ ከነበረው በተሻለና በተለይ በርካታ ተሳታፊዎች በሚገኙበት መስከረም 13 ዓርብ ቀን መነሻውን ከኮሎኔል በዛብህ ጵጥሮስ አደባባይ ያደረገ የአምስት ኪ/ሜ ሩጫ እንደሚደረግ በመጠቆም ፣

አድሱ ዓመት የሠለም፣ የአንድነት፣ የአብሮነት፣ የልማት፣ የዕድገት፣ የስኬትና የብልጽግና እንዲሆን መልካም ምኞታቸውን አስተላለፈዋል ፡፡

በሰለሞን ወልዴ

Share this Post