የመምሪያ ኃላፊዎች እንኳን ለ2015 ዓመት ለ"ያሆዴ" በዓል በሰላም አደረሳችሁ መልዕክት አስተላልፏል።

የሀዲያ ዞን የፐብሊክ ሰርቪስና ሰው ሀብት ልማት መምሪያ ኃላፉ ወ/ሪት ገነት ሙሉጌታ ተገልጋዩን ማህበረሰብ በቅንነት ፤ በታማኝነት ከአድልዎ በፀዳና ውጤታማ የሆነ አገልግሎት በመስጠት ተገልጋዩን ማርካት የሚጠበቅ መሆኑን በማስገንዘብ ፦

በዚህ አዲስ ዓመት የሚሰጠው አገልግሎት ደረጃውን የጠበቀ እንዲሆን በማድረግ ለዞናችን ለሁለተናዊ ዕድገት የበኩላችንን መወጣት አለብን ብለዋል።

የሀዲያ ዞን ውሃ፣ ማዕድንና ኢነርጂ መምሪያ ኃላፊ አቶ መለሠ ኃይሌ እና ቴ/ሙያ መምሪያ ተወካይ አቶ ፈለቀ ከበደ እንደተናገሩት የ"ያሆዴ " በዓል የሀዲያ ብሔር ማንነት መገለጫና የብሔሩ የዘመን መለወጫ በዓል ሲሆን በየዓመቱ በብሔሩ ተወላጆች ዘንድ በልዩ ድምቀት የሚከበር ተወዳጅ በዓል መሆኑን ጠቅሰው

አዲሱ ዓመት የሠላም፣ የአንድነት፣ የአብሮነት፣ የልማት፣ የዕድገት፣ የስኬትና የብልጽግና እንዲሆን መልካም ምኞታቸውን አስተላለፈዋል ፡፡

በጫኬቦ ኤርጫፎ

Share this Post