የሆሳዕና ከተማ አስተዳደር የመንግስት ኮሙኒኬሽን ጉዳዮች ጽ/ቤት ጥቅምት 23/2015 ዓ.ም
የሆሳዕና ከተማ ምክር ቤት ዋና አፈ-ጉባኤ ወ/ሮ ሙሉነሽ ሴድሶ የ2015 የ1ኛ ሩብ ዓመት ለፎረም በቀረበው ዕቅድ ክንውን ሪፖርትን አስመልክቶ የከተማችን ዕድገት ለማፋጠን፣ድህነትና ኋላቀርነትን ለማስወገድ እየተደረገ ያለው ርብርብ ወደ ተሻለ ምዕራፍ የሚያሸጋግሩ በርካታ ተግባራት መከናወኑን ጠቁመዋል ።
አክለውም በየደረጃው የሚገኙ ምክር ቤቶች ተጠሪነታቸው ለህገ-መንግሥቱና ለወካዩ ህዝብ ቢሆንም ምክር ቤቶች በጋራ ጉዳዮቻቸው ላይ የሚመካከሩበትና የልምድ ልውውጥ የሚያካሄዱበት እንድሁም የቀበሌው ምክር ቤቶች ከከተማው ም/ቤቶች ጋር ትስስር የሚፈጥሩበት የጋራ መድረክ መሆኑን ገልፀዋል ።
የከተማና የቀበሌ ምክር ቤቶች የ2015 የ1ኛ ሩብ ዓመት ዕቅድ አፈጻጸም ሪፖርት ለፎረም ምክር ቤት አባላት ቀርቦ ሰፊ ውይይት ተደርጎ መጽደቁንም ገልጸዋል ።
የከተማው ምክር ቤት ም/አፈ-ጉባኤ ወ/ሮ ደሰለች ገብሬ በበኩላቸው የየቀበሌው የሩብ ዓመት ዕቅድ አፈጻጸም ሪፖርቶች በመልካም አስተዳደር ፣ በከተማ ግብርና፣ኢንተርፕራይዝ
፣ በትምህርት ፣ በጤና ፣ በሰላምና ፀጥታ በሌሎችም ጉዳዮች ላይ ባተኮረ ዕቅድ አፈጻጸም ሪፖርት ቀርቦ የውይይት መድረክ ማስኬድ ተችሎዋል ስሉ ጠቅሰዋል ።
በመጨረሻም በ2014 በጀት ዓመት በአጠቃላይ ሥራ አፈጻጸም ላይ ከስድስቱም ቀበሌያት መካከል 1ኛ ሄጦ ቀበሌ 2ኛ ሴች ዱና ቀበሌ 3ኛ አራዳ ቀበሌ ሲሆን ከከተማው ም/ቤት ባለሙያዎች መካከል 1ኛ ለአቶ ገበየሁ ወ/የስ 2ኛ ወ/ሮ አልማዝ አንሽሶ 3ኛ ለአቶ መለሰ አባይነህ ዮሚሶ ባለሙያዎች ግንባር ቀደመ ለሆኑት የዕውቅና ሰርተፍኬትና የኮ/ባዛብህ ጴጥሮስ ሐውልት ፎቶግራፍ ተሰጥተዋል ።