በሆሳዕና ከተማ ኢንተርፕራይዝና ኢንዱስትሪ ልማት ጽ/ቤት በ2015 ዓ.ም 10ሺ 126 በዝቅተኛ የኑሮ ደረጃ ላይ የሚገኙ የህብረተሰብ ክፍሎች በምግብ ዋስትና የሴፍትኔት ኘሮግራም በማሳተፍ ተጠቃሚ ለማድረግ የሚያስችል ዝግጅት እያደረገ መሆኑን ገለፀ ።

በሆሳዕና ከተማ ኢንተርፕራይዝና ኢንዱስትሪ ልማት ጽ/ቤት በ2015 ዓ.ም 10ሺ 126 በዝቅተኛ የኑሮ ደረጃ ላይ የሚገኙ የህብረተሰብ ክፍሎች በምግብ ዋስትና የሴፍትኔት ኘሮግራም በማሳተፍ ተጠቃሚ ለማድረግ የሚያስችል ዝግጅት እያደረገ መሆኑን ገለፀ ።

በዛሬው ዕለት ከሁሉም ቀበሌዎች ለተወጣጡ መልማይ ኮሚቴዎች ስልጠና ተሰጥቷል ።

የከተማው መንግስት ኮሙኒኬሽን ጉዳዮች ጽ/ቤት ነሐሴ 10/2014 ዓ.ም

የከተማው ምክትል ከንቲባና ኢንተርፕራይዝ እና ኢንዱስትሪ ልማት ጽ/ቤት ኃላፊ አቶ በየነ ሸንቆ ስልጠናውን በንግግር ሲከፍቱ መልማይ ኮሚቴዎች ከስልጠናው ባገኙት ዕውቀት በመታገዝ የድሃ ድሃ የሆኑ ግለሰቦች ቤት ለቤት ክትትል በማድረግ በትክክል ሀላፊነታቸውን እንዲወጡ አሳስበዋል ።

የከተማው ኢንተርፕራይዝ እና ኢ/ልማትጽ/ቤት ም/ ኃላፊ እና የማንፋክቸሪንግ ዘርፍ ኃላፊ አቶ ሙላቱ ሱሌ የሥራ ዕድል ፈጠራና ምግብ ዋስትና ዘርፍ ኃላፊ አቶ ፀጋዬ መንዶዕሎ በየበኩላቸው እንደገለጹት በከተማው ሴፍትኔት ፕሮግራም የድሃ ድሃ የሆኑ የህብረተሰብ ክፍሎች በሂደት ራሳቸውን እንዲችሉ ለማገዝ ባለፈው ዓመት በአራዳና ቦቢቾ ቀበሌዎች 2 ,664 ተጠቃሚዎች በማሳተፍ ተጀምሯል ።

አክለውም በከተማው በ2015 ዓ.ም በሁሉም ቀበሌዎች በሴፍቲኔት ከሚሳተፉ 10ሺ 126 ጠቃሚዎች መካከል 1620 የሚሆኑት አቅመ ደካሞች ቀጥታ ተጠቃሚዎች ሲሆኑ ቀሪዎቹ በየአካባቢያቸው በተለያዩ የልማት ሥራዎች በማሳተፍ ድጋፍ እንደሚደረግላቸው ገልፀዋል ።

የልማታዊ ሴፍቲኔት ተጠቃሚዎች በተለያዩ የልማት ሥራዎች በመሳተፍ ከሚያገኙት ገቢ 20 በመቶ እንዲቆጥቡ በማድረግ በሂደት ራሳቸውን እንዲችሉ እየተሠራ መሆኑንም ኃላፊዎቹ ጨምረው ገልፀዋል ።

Share this Post