በዞኑ በክረምት የወጣቶች በጎ ፈቃድ አገልግሎት የ297 አረጋውያንና አቅመ ደካሞች ቤት ግንባታና እድሳት ተከናውኗል _የሀዲያ ዞን ወጣቶችና ስፖርት መምሪያ

ጥቅምት 23/2015 ዓ.ም (የሀዲያ ዞን መ/ኮ/ጉ/መምሪያ)

በሀዲያ ዞን በክረምት የወጣቶች በጎ ፈቃድ አገልግሎት የ297 አረጋውያንና አቅመ ደካሞች ቤት ግንባታና እድሳት መከናወኑን የዞኑ ወጣቶችና ስፖርት መምሪያ አስታወቀ

በዞኑ የ2014 ዓ.ም የክረምት ወራት የወጣቶች በጎ ፈቃድ አገልግሎት ማጠቃለያ መርሃግብር ተካሂዷል።

በመርሃግብሩ ላይ ተገኝተው ንግግር ያደረጉት የሀዲያ ዞን ዋና አስተዳዳሪ አቶ አብርሃም መጫ በአሁኑ ወቅት የሀገራችን ሉአለዊነት እየተከበረ ያለው በወጣቶች ሚና ነው በማለት የህባችን ድህነት ችግር መፍትሔ እውን የሚሆነው በወጣቶች ተሳትፎ ነው ብለዋል።

ወጣቶች በአሮንጓዴ ዐሻራ፣ በማህበራዊ ደህንነት ድጋፍና እንክብካቤ፣ በመንገድ ደህንነትና ትራፊክ እንዲሁም ለአቅመ ደካሞች በጎ ፈቃድ አገልግሎት መስጠት ለሌላ ህብረተሰብ መኖር እንደሆነ ገልፀዋል።

በሁሉም ዘርፍ በስብዕና የተገነባ፣ሌብነትን የሚፀየፍ ወጣቶች በመፍጠር አካባቢውንና ሀገርን በልማት የመቀየር ሚና ከፍተኛ መሆኑን አስረድተዋል ።

የወጣቶችን ተሳትፎ በፖላቲካ፣ በኢኮኖሚና በማህባራዊ ዘርፍ በማረጋገጥ ሁለተንታናዊ ተጠቃሚ ማድረግ ይገባል ብለዋል።

የሀዲያ ዞን ወጣቶችና ስፖርት መምሪያ ኃላፊ አቶ ተሻለ ደሳለኝ በበኩላቸው ወጣቶች በጎ ፈቃድ አገልግሎት ግለሰቦች ከሳቢያዊነት አማላካከት በመነሳት ጊዜያቸውን፣ ጉልበታቸውን፣ ገንዘባቸውንና ዕውቀታቸውን በመጠቀም የብዙዎቹን ህይወት እየቀየሩ ይገኛል ብለዋል።

በዞናችን የወጣትች በጎ ፈቃድ አገልግሎት በተለያዩ መስክ እየዳበረ በመምጣቱ በርካታ እርዳታ የሚሹ ዜጎች ተጠቃሚ መሆን ችለዋል ነው ያሉት።

እንደ ኃላፊው ገለጻ ባለፈው ዓመት በዞኑ በአስራ አራት መስኮች ከ2 መቶ 11 ሺህ በላይ ወጣቶች መሳተፉን ገልጸዋል።

ለአብነት በዞኑ በወጣቶች የክረምት በጎ ፈቃድ አገልግሎት ከ195 የአረጋውያንና አቅመ ደካሞች ቤት እድሳትና ጥገና የተደረገ ሲሆን 102 አድስ ቤት ግንባታ ተደርጓል ብለዋል።

እንዲሁም ለ3 ሺህ 4 መቶ 10 እገዛ ለሚያስፈልጉ ተማሪዎች የትምህርት ቁሳቁስ ድጋፍ መከናወኑን አስረድተዋል።

በአጠቃላይ በዓመቱ በወጣቶች የክረምት በጎ ፈቃድ አገልግሎት በተከናወኑ ተግባራት ከመንግስትና ከህብረተሰቡ ልወጣ የሚችለውን 137 ሚሊየን 701 ሺህ 321 ብር ባላይ ወጪ መደን መቻሉን ጠቁመዋል።

የመርሃግብሩ ተሳታፊዎችም በሰጡት አስተያየት በህዝብ አገልጋይነት የተነፁ ወጣቶች መፍጠር የሁላችንም ትኩረት ሊሆን ይገባል።

ከዚህም ጎን ለጎን የወጣቶች ሁለንተናዊ ጥቅም ለማረጋገጥ የወጣቶች ስብዕናና አማለካካት ማጎልበት በትኩረት ሊሰራ ይገባል ብለዋል።

በመድረኩም የ2015 የወጣቶች በጎ ፈቃድ አገልግሎት ዕቅድ ቀርቦ ውይይት ተደርጓል።

በደገለ ባምቦሬ

 

 

 

 

 

Share this Post