በሆሳዕና ከተማ አስተዳደር ትምህርት ጽ/ቤት በሀገር ደረጃ ሙሉ ትግበራ በሚሰጠው አድሱ ስርአተ ትምህርት መምህራንና የትምህርት አመራሩን የአዲስ መጽሐፍ ትውውቅ ስልጠና መድረክ ለ3 ተከታታይ ቀናት የሚቆይ የስልጠና ተጀመረ ።

የሆሳዕና ከተማ አስተዳደር መንግስት ኮሙኒኬሽን ጉዳዮች ጽ/ቤት መስከረም 30/2015 ዓ.ም

የሆሳዕና ከተማ አስተዳደር ም/ከንቲባና ኢን/ ኢን/ልማት ጽ/ቤት ኃላፊ አቶ በየነ ሸንቆ

ና የከተማው ትምህርት ጽ/ቤት ኃላፊ አቶ አዳነ ዘመድኩን በየበኩላቸው እንደገለፁት

በከተማው የሚገኙ የግልና የመንግስት የ1ኛ ደረጃ ትምህርት ቤቶች አዲሱ ሥርአተ ትምህርት መጽሐፍ ትውውቅ በሚደረግበት ቀን በታሪክ የመጀመሪያ የሆነው የ12ኛ ክፍል ተመሪዎች ዩንቨርሲቲ መግቢያ ፈተና በሚሰጥበት ዕለት መሆኑ ልዩ ያደርጋል ስሉ ገልፀዋል ።

አክለውም ኃላፊዎቹ የትምህርት ጥራት ለማስጠበቅ ብቸኛ መንገድ መምህራን በአዲሱ ስርአተ ትምህርት የተዘጋጀውን መጽሐፍት የመማር ማስተማር ተግባራዊ ማድረግ አለባት ስሉ ተናግረዋል ።

በመጨረሻም በከተማው የሚገኙ የግል ት/ቤቶች የከዚህ ቀደም ይሰጡ የነበረውን ትምህርት በአዲሱ ስርአተ ትምህርት ተክተው ሁሉም ት/ቤቶች በሀገሪቱ ተቀርጾ ባለው ስርአተ ትምህርት ብቻ መተግበር እንደሚገባ አሳስበዋል ።

Share this Post