የሰላም ሚኒስቴር ከዋቸሞ ዩኒቨርሲቲ ጋር በመተባበር ለ4ኛ ዙር ያሰለጠናቸዉን ብሔራዊ የበጎ ፍቃድ ማህብረሰብ ልማት አገልግሎት ሠልጣኞችን አስመረቀ።

የሰላም ሚኒስቴር ከዋቸሞ ዩኒቨርሲቲ ጋር በመተባበር 4 ዙር ያሰለጠናቸዉን ብሔራዊ የበጎ ፍቃድ ማህብረሰብ ልማት አገልግሎት ሠልጣኞችን አስመረቀ።

 የሆሳዕና ከተማ አስተዳደር መንግስት ኮሙኒኬሽን ጉዳዮች /ቤት እንደዘገበዉ።

"በጎነት ለአብሮነት" በሚል መሪ ቃል 2000 በላይ በጎ ፍቃደኛ ወጣቶችን አስመርቋል።

በምረቃዉ የተገኙት የዋቸሞ ዩኒቨርስቲ ፕሬዝደንት / ሀብታሙ አበበ በምርቃት ፕሮግራም ላይ ባስተላለፉት መልዕክት የሰላም አምባሳደር ወደሆነዉ ዋቸሞ ዩኒበርስቲ እንኳን ደህና መጣችሁ ቆያችሁ ካሉ በኋላ 2017 / ከኢትዮጵያ ምርጥ አስር ዩኒቨርስቲ አንዱና የልሂቃን መፍለቂያ ሆኖ ማየትን ራዕይ አንግቦ እየተሰራ መሆኑን ገልፀዉ።

ፕሬዝደንቱ አክለዉም የበጎ ፍቃድ ማህበረሰብ አገልግሎት ደመወዝ የማይገኝበት ባይሆንም ትልቅ የአይምሮ እርካታ የሚሰጥ ትልቅ ተግባር በመሆኑ ተመራቂዎች የሰላም ሚኒስቴር በሚያስቀምጠዉ አቅጣጫ በመንቀሳቀስ የሚጠበቅባችሁን ልትወጡ ይገባል ብለዋል።

የእለቱ የክብር እንግዳ የሰላም ሚኒስቴር ሚኒስትር /ቤት ኃላፊ / ሂሩት ድሌቦ በበኩላቸዉ የብሔራዊ በጎ ፍቃድ ማህበረሰብ ልማት ፕሮግራም ተሳታፌ በመሆን ሀገራችሁንና ወገናችሁን በበጎ ፍቃድ በማገልገል በሕዝባችን መካከል ያለዉን ወንድማማችነትና የእርስ በርስ ትስስር እንዲጎለብትና በማህበረሰቡ ዉስጥ የሚታዩ ችግሮች በጋራ በመቅረፍ የወገን አለኝታና መከታ ለመሆን የተዘጋጃችሁ ተመራቂ ወጣቶች እንኳን ደስ አላችሁ ብለዋል።

አክለዉ የሰላም ሚኒስትር በሀገራችን ሁለንተናዊ ሰላም እንዲረጋገጥ ለማድረግ እየሰራ መሆኑን ወጣቱ ትዉልድ ሀገራችንና ማህበረሰባችንን እንዲያዉቅ፣ እንዲረዳ የሀገር ፍቅር ስሜትን በዉስጣቸዉ ለማስረፅ ያስቻለና ተመራቂዎች በቂ የሆነ እዉቀት የጨበጣችሁበትና በቀጣይ በምትሰማሩበት ማህበረሰብ ታዳጊዎቻችንና ወጣቶች መልካም አርአያ ማሳየት እንደሚገባ አሳስበዋል።

4 ዙር ብሔራዊ የበጎ ፍቃድ ማህብረሰብ ልማት አገልግሎት ተመራቂዎች በበኩላቸዉ በወሰዱት ስልጠና ከፍተኛ የሆነ የሀገር ፍቅር ስሜት እንዳደረባቸዉና ስለ በጎ ፍቃድ አገልግሎ በቂ ግንዛቤ ያገኙበት ለሰላም እሴት ግንባታ ግንዛቤ ያገኙበት እንደሆነ ገልፀዋል።

Share this Post